በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“መታዘዝ ያለብን ማንን ነው?” የሚለው ንግግር አያምልጥህ!

“መታዘዝ ያለብን ማንን ነው?” የሚለው ንግግር አያምልጥህ!

“መታዘዝ ያለብን ማንን ነው?” የሚለው ንግግር አያምልጥህ!

ብዙ ሰዎች መታዘዝ የሚለው ሐሳብ ራሱ አይጥማቸውም። ‘ደስ የሚለኝን ማድረግ እንጂ ማንም ሰው በዚህ ግባ በዚህ ውጣ እንዲለኝ አልፈልግም’ የሚለው አመለካከት በጣም የተለመደ ሆኗል። እውነታው ግን ሁላችንም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ለታዛዥነት ከፍተኛ ግምት እንደምንሰጥ የሚያሳይ ነው። አንድን የማስጠንቀቂያ ምልክት ስትታዘዝ ወይም መመሪያዎችን ስትከተል ይብዛም ይነስም ታዛዥነት እያሳየህ ነው። የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ያወጧቸውን ሕግጋት መታዘዝ በሰው ልጆች ኅብረተሰብ መካከል ሥርዓትና ሰላም እንደሚያሰፍን ማን ሊክድ ይችላል? ሁሉም ሰዎች የትራፊክ ደንቦችን አንታዘዝም ቢሉ ምን ሊከሰት እንደሚችል እስቲ ገምት!

ይሁን እንጂ ሰዎች በሰዎች ላይ ገዥዎች መሆናቸው ሁልጊዜ ጥሩ ውጤት ይኖረዋል ማለት አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ ከረጅም ጊዜያት በፊት ‘ሰው ሰውን ለመጒዳት ገዥ ይሆናል’ ብሎ ነበር። (መክብብ 8:9) የእኛን አመኔታም ሆነ ታዛዥነት ማግኘት የሚገባው ገዥ ይኖር ይሆን? ካለስ፣ እንዴት ልናውቀው እንችላለን? ከአገዛዙስ ምን ልንጠብቅ እንችላለን? እነዚህ ጥያቄዎች “መታዘዝ ያለብን ማንን ነው?” በሚለው ልብ ቀስቃሽ ንግግር ላይ መልስ ያገኛሉ። ይህ የሕዝብ ንግግር የይሖዋ ምሥክሮች ከዚህ ወር ጀምሮ በሚያደርጓቸው የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ይሰጣል። በመቶ የሚቆጠሩት እነዚህ ስብሰባዎች በዓለም ዙሪያ ይካሄዳሉ። በአቅራቢያህ ስብሰባው የት እንደሚካሄድ ለማወቅ እንድትችል በአካባቢህ የሚገኙትን የይሖዋ ምሥክሮች ጠይቅ፤ አሊያም ገጽ 5 ላይ የሰፈሩትን አድራሻዎች በመጠቀም ወደዚህ መጽሔት አዘጋጆች መጻፍ ትችላለህ።