በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኤድስ በአፍሪካ—በአዲሱ ሺህ ዓመት ተስፋ ሰጪ ነገር ይኖር ይሆን?

ኤድስ በአፍሪካ—በአዲሱ ሺህ ዓመት ተስፋ ሰጪ ነገር ይኖር ይሆን?

ኤድስ በአፍሪካ—በአዲሱ ሺህ ዓመት ተስፋ ሰጪ ነገር ይኖር ይሆን?

በዛምቢያ የንቁ! መጽሔት ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

በአፍሪካ እየተዛመተ ባለው በኤድስና በአባለ ዘር በሽታዎች ላይ በሚነጋገረው 11ኛው ዓለም ዓቀፍ ጉባኤ ላይ ለመገኘት ባለፈው መስከረም ከተለያዩ የአፍሪካ አገሮች የመጡ ልዑካን ሉሳካ ዛምቢያ ውስጥ ተሰብስበው ነበር። የዚህ ጉባኤ ዋና ዓላማ በአፍሪካ ያለውን የኤድስ ሥርጭት እንዴት መግታት እንችላለን? ለሚለው ጥያቄ መልስ በማፈላለግ ረገድ ክፍለ አህጉራዊ ትብብር እንዲኖር ማበረታታት ነበር።

የዛምቢያ የጤና ሚኒስትር የሆኑት ፕሮፌሰር ንካንዱ ሉኦ የበሽታው መዛመት በአፍሪካም ሆነ በቀረው ዓለም በሚገኙ ታዳጊ አገሮች ውስጥ ያለበትን ሁኔታ አስመልክተው ሲናገሩ ሁኔታው “እጅግ አሳሳቢ” መሆኑን ከገለጹ በኋላ “በጤና እንዲሁም በሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ረገድ ያገኘነው እድገት ባለበት እንዲሄድ እንዲያውም እንዲቀለበስ አድርጓል” ብለዋል።

ደምን በተመለከተ ሊወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄ የተካሄደ አውደ ጥናት ኤድስ ደምን በደም ሥር በመስጠት ሲተላለፍ እንደቆየ አረጋግጧል። በዓለም ጤና ድርጅት ሥር ብለድ ሴፍቲ ዩኒት የተባለው ክፍል ተወካይ የሆኑ አንድ ዶክተር እንደጠቆሙት:- “በሽታው በኤች አይ ቪ ከተለከፈ ሰው ጋር የፆታ ግንኙነት በማድረግ የማይተላለፍበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል። በኤድስ የተበከለን ደም በደም ሥር የወሰደ ሰው ግን በበሽታው ከመለከፍ ፈጽሞ ሊያመልጥ አይችልም!” እኚህ ዶክተር “ደምን በተመለከተ ሊወሰድ የሚገባው የተሻለው የጥንቃቄ ዓይነት ደምን በደም ሥር አለመስጠት ነው” በማለት የተናገሩት ያለምክንያት አይደለም።

የሕክምና ወጪ እጅግ መናሩ በኤድስ የተለከፉ ሰዎች ሕክምና እንዳያገኙ እንቅፋት እንደሆነ የሉሳካው ጉባኤ አጽንኦት ሰጥቶ ተነጋግሮበታል። ለምሳሌ ያህል የከተማ ነዋሪ የሆነ አንድ ኡጋንዳዊ አማካይ የወር ገቢው 200 የአሜሪካ ዶላር ነው። ይሁን እንጂ የቫይረሱን ስርጭት በሚገቱ መድሃኒቶች ሕክምና ለማግኘት በወር 1, 000 የአሜሪካ ዶላር መክፈል ይጠይቃል!

በአዲሱ ሺህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የኤድስን ስርጭት ለመግታት የሚያስችል ቀላል መፍትሔ ይገኛል ተብሎ እንደማይታሰብ የሉሳካው ጉባኤ አመላክቷል። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ሁሉም በሽታዎች በመጨረሻ ፈውስ የሚያገኙት እሱ በሚያመጣው አዲሱ ሥርዓት ውስጥ ‘የሚቀመጥ ሁሉ ታምሜያለሁ እንደማይል’ ቃል በገባው ፈጣሪ በይሖዋ አምላክ አማካኝነት እንደሆነ ይገነዘባሉ።​—⁠ኢሳይያስ 33:​24

[በገጽ 20 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ፕሮፌሰር ንካንዱ ሉኦ

[ምንጭ]

Photograph by permission of E. Mwanaleza, Times of Zambia