በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ዓለማችን የተለየች ትሆን ነበር’

‘ዓለማችን የተለየች ትሆን ነበር’

‘ዓለማችን የተለየች ትሆን ነበር’

ባለፈው ነሐሴ ወር በሞስኮ የይሖዋ ምሥክሮችን የአውራጃ ስብሰባ ለመሰረዝ ተደርጎ የነበረው ጥረት ከፍተኛ ትኩረት ስቦ ነበር። አንድሬይ ዞሎቶቭ ጁንየር ነሐሴ 21, 1999 በወጣው ዘ ሞስኮ ታይምስ ላይ “የስፖርት ሥፍራው ምክትል ዲሬክተር የሆኑት ቭላድሚር ኮዝርዬቭ አስተዳደሩ የይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ መካሄዱን አይቃወምም ሲሉ ተናግረዋል። [ስብሰባው እንዲሰረዝ የሚያዘው] መመሪያ ከየት እንደመጣ የማያውቁ መሆኑን ገልጸዋል” ሲል ዘግቧል።

ከአንድ ሳምንት በኋላ ዘ ሞስኮ ታይምስ አትሞ ባወጣው አንድ ደብዳቤ ላይ አንድ አንባቢ ጋዜጣው “ከወገናዊነት ስሜት ፍጹም ነፃ የሆነውን” ጽሑፍ በማውጣቱ ምስጋናቸውን የገለጹ ሲሆን ጉዳዩ “አንባብያን ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው ነው” ብለዋል። “የይሖዋ ምሥክሮች ለዓመታዊው ስብሰባቸው ሲዘጋጁ የገጠሟቸውን ከባድ ችግሮች የሚገልጸው ዘገባችሁ የደረሰባቸውን በደል [አጋልጧል]” ሲሉ ተናግረዋል።

በመቀጠልም የደብዳቤው ጸሐፊ እንዲህ ሲሉ ገልጸዋል:- የይሖዋ ምሥክሮች “በዓለም ዙሪያ (አሁን ደግሞ በሩስያ) በደንብ የታወቁ ናቸው . . . በቀላሉ የሚቀረቡ፣ የሚወደድ ባሕርይ ያላቸው፣ ደጎችና የዋሆች . . . ናቸው። በሌሎች ሰዎች ላይ ምንም ዓይነት አሉታዊ ተጽዕኖ የማያሳድሩ ከመሆናቸውም በላይ የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና፣ የቡዲዝምም ሆነ የሌላ የማንኛውም ሃይማኖት ተከታይ ከሆኑ ሰዎች ጋር ምንጊዜም ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚሹ ሰዎች ናቸው። ጉቦኞች፣ ሰካራሞች ወይም የአደገኛ ዕፅ ሱሰኞች በመካከላቸው አይገኙም። ይህ የሆነበት ምክንያት ግልጽ ነው:- በሚያደርጉትና በሚናገሩት ነገር ሁሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረቱት ጽኑ እምነቶቻቸው ለመመራት ጥረት ስለሚያደርጉ ነው። በዓለም ዙሪያ ያሉት ሰዎች በሙሉ የይሖዋ ምሥክሮች እንደሚያደርጉት ቢያንስ ቢያንስ መጽሐፍ ቅዱስ በሚለው መሠረት ለመመላለስ ጥረት ቢያደርጉ በጭካኔ የተሞላችው ዓለማችን ፈጽሞ የተለየች ትሆን ነበር።”

የይሖዋ ምሥክሮችን ቀረብ ብለው ያጠኑና በቀጥታ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር የተወያዩ ባለ ሥልጣኖች ከላይ ያለውን አባባል እውነትነት ያረጋግጣሉ። ለምሳሌ ያህል እነዚህ ባለ ሥልጣኖች በሩስያ ሴይንት ፒተርስበርግ ውስጥ የይሖዋ ምሥክሮች ይህን ውብ የሆነ አዲስ የትልቅ ስብሰባ አዳራሽ እንዲገነቡ ፈቃድ ሰጥተዋል። አዳራሹ ባለፈው መስከረም 18 ቀን ለይሖዋ አገልግሎት ሲወሰን በደስታ ስሜት የተዋጡ 2, 257 ሰዎች በቦታው ተገኝተው የነበረ ሲሆን ሌሎች 2, 228 ሰዎች ደግሞ በሴይንት ፒተርስበርግ በሚገኙ የመንግሥት አዳራሾች ውስጥ እንዲሁም በአቅራቢያው ባለችው በሶልኔችኖዬ በሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ሆነው ፕሮግራሙን ተከታትለዋል።