መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥቅምት 2017

ይህ እትም ከኅዳር 27 እስከ ታኅሣሥ 24, 2017 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

የሕይወት ታሪክ

ይሖዋ የሚጠይቀንን ማድረግ በረከት ያስገኛል

በ1952 ኦሊቭ ማቲውስና ባለቤቷ ወደ አየርላንድ ተዛውረው በአቅኚነት እንዲያገለግሉ የቀረበላቸውን ግብዣ በፈቃደኝነት ተቀብለዋል። ይሖዋ የባረካቸው እንዴት ነው?

“በተግባርና በእውነት” እንዋደድ

ፍቅራችን ከልብ የመነጨና ከግብዝነት ነፃ እንደሆነ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ሰላምን ሳይሆን ሰይፍን የሚያመጣው እውነት

ኢየሱስ ‘ሰይፍን እንደሚያመጣ’ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር? ይህስ በአንተ ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?

የአርማትያሱ ዮሴፍ ከእውነት ጎን ቆመ

የአርማትያሱ ዮሴፍ ማን ነው? ከኢየሱስ ጋር ምን ግንኙነት ነበረው? ደግሞስ የእሱን ታሪክ ማወቅህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

ዘካርያስ ካያቸው ራእዮች ምን ትምህርት እናገኛለን?

የሚበር ጥቅልል፣ በመስፈሪያ ውስጥ ያለች አንዲት ሴት እና የራዛ ዓይነት ክንፎች ያላቸው በነፋስ መካከል የሚወነጨፉ ሁለት ሴቶች። አምላክ ዘካርያስ እንዲህ ያሉ ራእዮችን እንዲያይ ያደረገው ለምንድን ነው?

ጥበቃ የሚያደርጉልን ሠረገሎችና አክሊል

የመዳብ ተራሮች፣ የውጊያ ሠረገሎች እንዲሁም ንጉሥ ሆኖ የተሾመ ሊቀ ካህናት። ዘካርያስ ያየው የመጨረሻ ራእይ በዛሬው ጊዜ ላሉ የአምላክ ሕዝቦች ምን ማረጋገጫ ይሰጣል?

ክርስቲያናዊ ደግነት ያስገኘው ውጤት

አንዲት ክርስቲያን ያሳየችው ደግነት ተቃዋሚ የነበረን አንድ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለመማር ያነሳሳው እንዴት ነው?

ይህን ያውቁ ኖሯል?

ኢየሱስ መሐላን ያወገዘው በየትኛው የአይሁዳውያን ልማድ የተነሳ ነው?