መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 2 2020 | የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ሰዎች ይህን ጥያቄ ሲጠይቁ ኖረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ ግልጽ መልስ ይሰጣል።

“መንግሥትህ ትምጣ”—የብዙዎች ጸሎት

የዚህን ጸሎት ትርጉም ለመረዳት የአምላክን መንግሥት በተመለከተ የየትኞቹን ጥያቄዎች መልስ ማወቅ ያስፈልገናል?

የአምላክ መንግሥት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

ፍጽምና የጎደላቸው ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ከሆነ ችግሮች መከሰታቸው አይቀርም።

የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ማን ነው?

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች፣ ወደፊት የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ የሚያስተዳድረውን ገዢ ለማወቅ የሚያስችሉ ምልክቶችን በዝርዝር ጽፈዋል። በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ እነዚህን መግለጫዎች የሚያሟላው አንድ ሰው ብቻ ነው።

የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛው መቼ ነው?

አንዳንድ የኢየሱስ ታማኝ ተከታዮችም ይህን ጥያቄ አንስተው ነበር። ኢየሱስ ለጥያቄያቸው ምን መልስ ሰጣቸው?

የአምላክ መንግሥት ምን ነገሮችን ያከናውናል?

ኢየሱስ በምድር ላይ ያሉትን ችግሮች ሊያስተካክል የሚችለው የአምላክ መንግሥት ብቻ እንደሆነ ያውቅ ነበር። የአምላክ መንግሥት እምነት እንድንጥልበት የሚያደርጉ ምን ነገሮችን ከወዲሁ አከናውኗል?

የአምላክን መንግሥት ለመደገፍ አሁኑኑ እርምጃ ውሰድ!

ኢየሱስ ተከታዮቹን ከሁሉ አስቀድመው የአምላክን መንግሥት እንዲፈልጉ አሳስቧቸዋል። ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ብዙዎች የአምላክ መንግሥት እንዲመጣ ይጸልያሉ፤ ሆኖም ይህ መንግሥት ምን እንደሆነና ምን ነገሮችን እንደሚያከናውን አስበህ ታውቃለህ?