በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመንግሥቱ ተስፋዎች ሲፈጸሙ ለመመልከት ትጓጓለህ?

ክፍል 7

የመንግሥቱ ተስፋዎች—ሁሉንም ነገር አዲስ ማድረግ

የመንግሥቱ ተስፋዎች—ሁሉንም ነገር አዲስ ማድረግ

አንድ ትልቅ የበሰለ ፖም ከዛፍ ላይ ቀጠፍክ። ፖሙን ወደ ቅርጫትህ ውስጥ ከመጨመርህ በፊት ወደ አፍንጫህ ስታስጠጋው ደስ የሚለው መዓዛው አወደህ። ለብዙ ሰዓታት ስትሠራ ብትቆይም ድካም አልተሰማህም። እናትህ ከሌሎች የቤተሰባችሁ አባላትና ሊያግዟችሁ ከመጡ ወዳጆቻችሁ ጋር እየተጫወተች በአቅራቢያህ ካለ ዛፍ ላይ ፖም ትሰበስባለች። እናትህ ወጣት ሆናለች፤ የአሁኑ መልኳ ከብዙ ዓመታት በፊት ሕፃን እያለህ የምታውቀው ዓይነት ነው። ይህች ሴት፣ ካለፈ ረጅም ጊዜ በሆነው በዚያ አሮጌ ሥርዓት ውስጥ አርጅታ ያየሃት እናትህ መሆኗን ማመን ከብዶሃል። በሕመም ምክንያት አቅሟ እየተዳከመ ሲሄድ፣ ከዚያም አጠገቧ ሆነህ እጇን እንደያዝክ በሞት ስታሸልብና አልቅሰህ ስትቀብራት ትዝ ይልሃል። አሁን ግን እሷና ሌሎች በርካታ ሰዎች ከሞት ተነስተውና ፍጹም ጤናማ ሆነው እየኖሩ ነው!

እንዲህ ያለ ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኞች ነን። ምክንያቱም አምላክ የሰጣቸው ተስፋዎች ምንጊዜም ይፈጸማሉ። የአምላክ መንግሥት እንደሚያከናውናቸው አስቀድሞ ከተነገሩት ተስፋዎች አንዳንዶቹ በቅርቡ እንዴት እንደሚፈጸሙና ይህ ሁኔታ ወደ አርማጌዶን ጦርነት የሚመራው እንዴት እንደሆነ በዚህ ክፍል ውስጥ እንመረምራለን። በተጨማሪም ከአርማጌዶን በኋላ መንግሥቱ የሚፈጽማቸውን አንዳንድ አስደሳች ተስፋዎች እንመለከታለን። የአምላክ መንግሥት መላውን ምድር ሲገዛና ሁሉንም ነገር አዲስ ሲያደርግ መመልከት ምንኛ አስደሳች ይሆናል!

በዚህ ክፍል ውስጥ

ምዕራፍ 21

የአምላክ መንግሥት ጠላቶቹን ያጠፋል

ለአርማጌዶን ጦርነት ከአሁኑ መዘጋጀት ትችላለህ።

ምዕራፍ 22

መንግሥቱ የአምላክ ፈቃድ በምድር ላይ እንዲፈጸም ያደርጋል

ይሖዋ የሰጣቸው ተስፋዎች እንደሚፈጸሙ እርግጠኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?