በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የበላይ አካሉ መልእክት

የበላይ አካሉ መልእክት

ይሖዋ አምላክንና ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን ለምትወዱ ሁሉ፦

ኢየሱስ “እውነትንም ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነፃ ያወጣችኋል” በማለት ተናግሯል። (ዮሐንስ 8:32) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን እውነት ለመጀመሪያ ጊዜ ስትማር ምን እንደተሰማህ እስቲ ለማስታወስ ሞክር። በሐሰት በተሞላ ዓለም ውስጥ እውነትን ማወቅ መቻል በጣም አስደሳች ነገር ነው!—2 ጢሞቴዎስ 3:1

ይሖዋ አምላክ እውነትን እንድናውቅ ይፈልጋል። እኛም ለሰዎች ፍቅር ስላለን ስለ እውነት ልንነግራቸው እንፈልጋለን። አምላክን ማገልገል ግን ከዚህ ያለፈ ነገር ማድረግን ይጨምራል። ለይሖዋ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጥልቅ አክብሮት ስላለን ለክርስቲያኖች በሚገባ መንገድ ለመኖር የምንችለውን ያህል መጣር ይኖርብናል። አምላክን እንደምንወደው ማሳየት የምንችልበትን አንዱን መንገድ ኢየሱስ ገልጿል። እንዲህ ብሏል፦ “እኔ የአብን ትእዛዛት ጠብቄ በፍቅሩ እንደምኖር እናንተም ትእዛዛቴን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።”—ዮሐንስ 15:10

ኢየሱስ አባቱን በጣም ይወደዋል፤ አባቱ የሚያዘውን ነገር ሁሉ ያደርጋል። እኛም በአኗኗራችን የኢየሱስን ምሳሌ የምንከተል ከሆነ ይሖዋ ይወደናል፤ እውነተኛ ደስታም እናገኛለን። ኢየሱስ “እነዚህን ነገሮች ስለምታውቁ ብትፈጽሟቸው ደስተኞች ናችሁ” በማለት ተናግሯል።—ዮሐንስ 13:17

ይህ መጽሐፍ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሚገኘው እውነት መሠረት ሕይወትህን ለመምራትና የአምላክ ወዳጅ ለመሆን እንዲረዳህ እንመኛለን። ለአምላክ ያለህ ፍቅር እያደገ እንዲሄድ እንዲሁም ‘የዘላለም ሕይወት የሚያስገኝልህን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት እየተጠባበቅክ ከአምላክ ፍቅር ሳትወጣ እንድትኖር’ ጸሎታችን ነው።—ይሁዳ 21

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል