ክፍል 1
እውነተኛው የዓለም ብርሃን
(የፊልሙ ርዝመት፦ 1:11:01)
ዮሴፍና ማርያም ኢየሱስን የማሳደግ ልዩ አደራ ተሰጣቸው። በተጨማሪም በዚህ ክፍል ላይ የሚከተሉትን ዘገባዎች ተመልከት፦
ቃል በመጀመሪያ ከአምላክ ጋር ነበር፤ ቃልም አምላክ ነበር (ዮሐንስ 1:1, 2)
አምላክ ሌሎች ነገሮችን ሁሉ የፈጠረው በቃል በኩል ነው (ዮሐንስ 1:3ሀ)
ሕይወት እና ብርሃን ወደ ሕልውና የመጡት በቃል አማካኝነት ነው (ዮሐንስ 1:3ለ, 4)
ጨለማው ብርሃኑን አላሸነፈውም (ዮሐንስ 1:5)
ሉቃስ ዘገባውን ያጠናቀረበትን መንገድና የጻፈበትን ምክንያት ለቴዎፍሎስ ገለጸ (ሉቃስ 1:1-4)
ገብርኤል ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መወለድ አስቀድሞ ተናገረ (ሉቃስ 1:5-25)
ገብርኤል ስለ ኢየሱስ መወለድ አስቀድሞ ተናገረ (ሉቃስ 1:26-38)
ማርያም ዘመዷን ኤልሳቤጥን ለመጠየቅ ሄደች (ሉቃስ 1:39-45)
ማርያም ይሖዋን ከፍ ከፍ አደረገች (ሉቃስ 1:46-56)
የዮሐንስ መወለድ እና ስሙ የወጣበት መንገድ (ሉቃስ 1:57-66)
ዘካርያስ የተናገረው ትንቢት (ሉቃስ 1:67-80)
ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ፀነሰች፤ ዮሴፍ የሰጠው ምላሽ (ማቴዎስ 1:18-25)
ዮሴፍ እና ማርያም ወደ ቤተልሔም ሄዱ፤ ኢየሱስ ተወለደ (ሉቃስ 2:1-7)
መላእክት ሜዳ ላይ ሲጠብቁ ለነበሩ እረኞች ተገለጡላቸው (ሉቃስ 2:8-14)
እረኞቹ ወደ ግርግም ሄዱ (ሉቃስ 2:15-20)
ኢየሱስን በይሖዋ ፊት ለማቅረብ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ (ሉቃስ 2:21-24)
ስምዖን ክርስቶስን የማየት መብት አገኘ (ሉቃስ 2:25-35)
ሐና ስለ ሕፃኑ ተናገረች (ሉቃስ 2:36-38)
ኮከብ ቆጣሪዎች ሊጠይቁት ሄዱ፤ ሄሮድስ ኢየሱስን ለማስገደል የጠነሰሰው ሴራ (ማቴዎስ 2:1-12)
ዮሴፍ፣ ማርያምንና ኢየሱስን ይዞ ወደ ግብፅ ሸሸ (ማቴዎስ 2:13-15)
ሄሮድስ በቤተልሔምና በአካባቢዋ የሚገኙትን ሕፃን ወንዶች ሁሉ አስገደለ (ማቴዎስ 2:16-18)
የኢየሱስ ቤተሰብ በናዝሬት መኖር ጀመረ (ማቴዎስ 2:19-23፤ ሉቃስ 2:39, 40)
የ12 ዓመቱ ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ውስጥ (ሉቃስ 2:41-50)
ኢየሱስ ከወላጆቹ ጋር ወደ ናዝሬት ተመለሰ (ሉቃስ 2:51, 52)
እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም የሚመጣበት ጊዜ ደርሶ ነበር (ዮሐንስ 1:9)

