በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ሕግ ነክ ማሳሰቢያዎች

ሕግ ነክ ማሳሰቢያዎች

Copyright

© 2014 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania, Inc. የባለቤቱ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

ይህን ድረ ገጽ ያዘጋጀውም ሆነ ክትትል የሚያደርግለት Watchtower Bible and Tract Society of New York, Inc. (ከዚህ በታች “የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር” ተብሏል) ነው። ሌላ መግለጫ ካልተሰጠ በቀር በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚገኘው ማንኛውም ጽሑፍና መረጃ Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania የተባለው ድርጅት አእምሯዊ ንብረት ነው።

የንግድ ምልክቶች

Adobe የሚለው መጠሪያና ዓርማው እንዲሁም Acrobat የሚለው መጠሪያና ዓርማው የAdobe Systems Incorporated የንግድ ምልክቶች ናቸው። iTunes እና iPod ደግሞ የApple Inc. የንግድ ምልክቶች ናቸው። በድረ ገጹ ላይ የሚገኙ ሌሎች የንግድ ምልክቶችና በሕግ የተመዘገቡ የንግድ ምልክቶች በሙሉ የተጠቀሰው ንግድ ምልክት ባለቤት ንብረቶች ናቸው።

የአጠቃቀም ውል እና ድረ ገጹን ለመጠቀም የሚሰጥ ፈቃድ

ይህን ድረ ገጽ በምትጠቀምበት ጊዜ የምትመራው በዚህ የአጠቃቀም ውል ነው። ይህን ድረ ገጽ መጠቀምህ በዚህ የአጠቃቀም ውል መሠረት ለመመራት ሙሉ በሙሉ መስማማትህን ያሳያል። በዚህ የአጠቃቀም ውል ወይም በውሉ ላይ ከተጠቀሱት ስምምነቶች ውስጥ በአንዱም ቢሆን የማትስማማ ከሆነ ድረ ገጹን መጠቀም የለብህም።

ድረ ገጹን በአግባቡ መጠቀም ሲባል ምን ማለት ነው? የቅጂ መብት ያላቸውን ምስሎች፣ ዲጂታል ጽሑፎች፣ መዝሙሮችና ሙዚቃዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ጽሑፎች፣ ቪዲዮዎች (ከዚህ በታች “የሕትመት ውጤቶች” ተብለዋል) ለግልና ከንግድ ውጪ ለሆነ ተግባር ለመጠቀም ከድረ ገጹ ላይ ማየት ማውረድና ማተም ትችላለህ፤ ይህን በምታደርግበት ጊዜ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትንም ሆነ በዚህ የአጠቃቀም ውል ውስጥ የተጠቀሱትን ሌሎች እገዳዎች የማክበር ግዴታ አለብህ። በመሆኑም የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ አይፈቀድም፦

  • ከድረ ገጹ ላይ የተወሰዱ የሕትመት ውጤቶችን በኢንተርኔት (ማለትም በማንኛውም ድረ ገጽ፣ ፋይሎችን በጋራ ለመጠቀም በሚያስችሉ ድረ ገጾች ወይም በማኅበራዊ ድረ ገጾች) ላይ ማስቀመጥ፤

  • ከዚህ ድረ ገጽ ላይ የተወሰዱ የሕትመት ውጤቶችን በሶፍትዌር ፕሮግራሞች ውስጥ በማንኛውም መልኩ ማካተት፤

  • በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚገኙትን የሕትመት ውጤቶች በማባዛት፣ በመገልበጥ፣ በመቅዳት ወይም በሌላ በማንኛውም መንገድ ለንግድ ወይም ገንዘብ ለማግኘት መጠቀም (ትርፍ የሚገኝበት ባይሆንም እንኳ)፤ ይህም በድረ ገጹ ላይ የተመሠረቱ፣ ከድረ ገጹ ጋር የተገናኙ ወይም ወደዚያ የሚመሩ አፕሊኬሽኖችን ወይም ፕሮግራሞችን (ቋሚ ወይም ተለዋዋጭ ቢሆኑም) ማሰራጨትን ይጨምራል፤

  • ከዚህ ድረ ገጽ ላይ ወይም ከዚህ ድረ ገጽ ጋር በተያያዘ በማንኛውም መልኩ መረጃዎችን ለመውሰድ የሚያገለግሉ (ይህም ስክሬፒንግ፣ ዳታ ማይኒንግ፣ ዳታ ኤክስትራክሽን፣ ዳታ ሃርቨስቲንግ እና ሌሎች ዘዴዎችን ይጨምራል) ሶርስ ኮዶችን፣ ቱሎችን ወይም ቴክኒኮችን ለመሥራት ወይም ለማሰራጨት ብሎ ድረ ገጹን መጠቀም፤

  • ድረ ገጹን ወይም ድረ ገጹ የሚሰጠውን አገልግሎት አላግባብ መጠቀም፤ ለምሳሌ ድረ ገጹን ወይም ድረ ገጹ የሚሰጠውን አገልግሎት ማስተጓጎል ወይም በግልጽ ከተቀመጠው መንገድ ውጪ ድረ ገጹን ወይም ድረ ገጹ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመጠቀም መሞከር፤

  • ድረ ገጹን በሚጎዳ ወይም ሊጎዳው በሚችል እንዲሁም ድረ ገጹ እንዳይሠራ ወይም ወደ ድረ ገጹ መግባት አስቸጋሪ እንዲሆን በሚያደርግ መንገድ ድረ ገጹን መጠቀም፤ ወይም በምንም መንገድ ቢሆን ሕገ ወጥ፣ ወንጀል፣ ማጭበርበር ወይም ጎጂ ለሆነ ዓላማ አሊያም ሕገ ወጥ፣ ወንጀል፣ ማጭበርበር ወይም ጎጂ ከሆነ ነገር ጋር ግንኙነት ላለው ተግባር መጠቀም፤

  • ድረ ገጹን ከግብይት ወይም ከሽያጭ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ተግባር መጠቀም።

የአጠቃቀም ውሉን ማፍረስ

በዚህ የአጠቃቀም ውል ውስጥ የተገለጹት የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ሌሎች መብቶች እንዳሉ ሆነው በውሉ ውስጥ ያለውን ማንኛውንም ስምምነት ብታፈርስ የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ተገቢ መስሎ የታየውን እርምጃ ሊወስድ ይችላል፤ ይህም ድረ ገጹን የመጠቀም መብትህን ማገድን፣ ድረ ገጹን እንዳትጠቀም መከልከልን፣ ድረ ገጹን ለመጠቀም በሚያስችልህ የአይፒ አድራሻ አማካኝነት የምትጠቀምባቸውን ኮምፒውተሮች ማገድን፣ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጡህን ድርጅቶች ድረ ገጹን ከመጠቀም እንዲያግዱህ መጠየቅን እና/ወይም ሕጋዊ እርምጃን መውሰድ ይጨምራል።

ለውጦች

የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ይህን የአጠቃቀም ውል አልፎ አልፎ ሊያሻሽለው ይችላል። የተሻሻለው የአጠቃቀም ውል በድረ ገጹ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ድረ ገጹን የሚጠቀሙ ሁሉ የሚመሩት በተሻሻለው ውል መሠረት ይሆናል። እባክህ ከወቅታዊው ውል ጋር በደንብ መተዋወቅ እንድትችል ይህን ገጽ በየጊዜው ተመልከተው።

ሕግ እና ሥልጣን

በተለያዩ ግዛቶች ውስጥ ያሉ ሕጎች ሊጋጩ ቢችሉም ይህ የአጠቃቀም ውል የጸና የሚሆነው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት በሆነው በኒው ዮርክ ሕግ መሠረት ይሆናል። ከዚህ የአጠቃቀም ውል ጋር የተያያዘ ማንኛውም ሕጋዊ እርምጃ የሚወሰደው ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የኒው ዮርክ ግዛት ላይ ሥልጣን ባለው የግዛቱ ወይም የፌዴራል ፍርድ ቤት መሆን ይኖርበታል።

ስምምነቶቹ የሚታዩት በተናጠል ነው

በአጠቃቀም ውሉ ውስጥ ከተጠቀሱት ስምምነቶች መካከል አንዱ፣ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ውድቅ ከሆነ፣ ተቀባይነት ካጣ ወይም ሕጋዊ እንዳልሆነ ከተወሰነ በውሉ ውስጥ የተጠቀሱት የተቀሩት ስምምነቶች የጸኑ እንደሆኑ ይቀጥላሉ። የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር በአጠቃቀም ውሉ ውስጥ የተጠቀሱትን ስምምነቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ አለመቻሉ እነዚህን ስምምነቶች ወይም ስምምነቶቹን የማስፈጸም መብቱን በገዛ ፈቃዱ ትቷል የሚያስብለው አይደለም።

አጠቃላይ ስምምነት

ይህ የአጠቃቀም ውል፣ ድረ ገጹን ከመጠቀም ጋር በተያያዘ በአንተ እና በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር መካከል የተደረገውን አጠቃላይ ስምምነት የያዘ ነው፤ እንዲሁም ይህን ድረ ገጽ ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል የተደረጉ ስምምነቶችን የሚሽር ነው።