የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

በjw.org ላይ ጥሩ የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት እንዲቻል ኩኪዎችንና ሌሎች ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎችን እንጠቀማለን። አንዳንድ ኩኪዎች ድረ ገጹ እንዲሠራ የግድ ስለሚያስፈልጉ መከልከል አይቻልም። አጠቃቀምህን ለማሻሻል ብቻ የምንጠቀምባቸውን ሌሎች ተጨማሪ ኩኪዎች መፍቀድ ወይም መከልከል ትችላለህ። ይህ መረጃ በፍጹም አይሸጥም ወይም ለንግድ ዓላማ አይውልም። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ገጽ ተመልከት፦ የኩኪዎችንና ተመሳሳይ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ዓለም አቀፍ ፖሊሲ በማንኛውም ጊዜ ምርጫዎችን ማስተካከል ከፈለግክ ይህን ገጽ ተጠቀም፦ የሚስጥር አጠባበቅ ማስተካከያ

እህት አና ማትቭዬቫ

ግንቦት 14, 2024 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 30, 2025
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—እህት የገንዘብ መቀጮ ተጣለባት | “ታዛዥነት በረከት ያስገኛል”

ወቅታዊ መረጃ—እህት የገንዘብ መቀጮ ተጣለባት | “ታዛዥነት በረከት ያስገኛል”

ሚያዝያ 29, 2025 በክራስናያርስክ ግዛት የሚገኘው የሌሶሲቢርስክ ከተማ ፍርድ ቤት፣ በእህት አና ማትቭዬቫ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ያስተላለፈ ሲሆን 400,000 ሩብል (4,876 የአሜሪካ ዶላር) የገንዘብ መቀጮ እንድትከፍል ወስኗል።

አጭር መግለጫ

እኛም እንደ አና የይሖዋን ማሳሰቢያዎች መስማት ሁሌም ደስታ እንደሚያስገኝልን እናውቃለን፤ ለዚህም አመስጋኞች ነን።—መዝሙር 119:111, 112

የክሱ ሂደት

  1. ኅዳር 25, 2021

    ፖሊሶች ለአንድ ዓመት ገደማ ወንድሞችን በስውር ሲቀዱ ከቆዩ በኋላ በሌሶሲቢርስክ የሚገኙ ስድስት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችን ፈተሹ፤ ከእነዚህ አንዱ የአና ቤት ነው

  2. ጥር 30, 2023

    የክስ ፋይል ተከፈተባት

  3. የካቲት 17, 2023

    የጉዞ ገደቦች ተጣሉባት

  4. ታኅሣሥ 29, 2023

    ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ