በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቅምት 6, 2017
አዲስ ነገር

“የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች” በተባለው ክፍል ላይ የተደረገ ለውጥ

“የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች” በተባለው ክፍል ላይ የተደረገ ለውጥ

jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ የሚገኘው “የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች” የተባለው ክፍል በአዲስ መልክ ተዘጋጅቷል። በውስጡ ያሉት ነገሮች በርዕሰ ጉዳይ ተከፋፍለው ስለተቀመጡ ለአጠቃቀም ይበልጥ ቀላል ሆኗል። የተደረጉት አንዳንድ ለውጦች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦

  • ታሪክ እና መጽሐፍ ቅዱስ” የሚለው አዲስ ንዑስ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስን እስከ ዘመናችን ጠብቆ ለማቆየት፣ ለመተርጎምና ለማሰራጨት ስለተደረጉት ጥረቶች እንዲሁም አዲስ የተገኙ ማስረጃዎች መጽሐፍ ቅዱስ ከታሪክ አንጻር ትክክል መሆኑን እያረጋገጡ ያሉት እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።

  • ሰላም እና ደስታ” የሚለው አዲስ ንዑስ ክፍል መጽሐፍ ቅዱስ በየዕለቱ የሚያጋጥሙህን ችግሮች መቋቋምና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ደስታ እና ሰላም ማግኘት እንድትችል የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

  • ሳይንስ እና መጽሐፍ ቅዱስ” የሚለው አዲስ ንዑስ ክፍል የፍጥረት ሥራዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ አንጻር ትክክል መሆኑን የሚያረጋግጡት እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው” የሚለው ንዑስ ክፍል ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ የተነሱ ጥያቄዎችን በቀላሉ ለማግኘት እንዲያስችል ለውጥ ተደርጎበታል።

  • ትዳር እና ቤተሰብ” የተባለው ንዑስ ክፍል “ለባለትዳሮችና ለወላጆች” የሚለውን ንዑስ ክፍል የሚተካ ነው፤ ይህ ክፍል፣ ትዳርን የተሳካ ማድረግና ልጆችን በጥሩ መንገድ ማሳደግ የሚቻልበትን መንገድ በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ጠቃሚ ምክር ይዟል።