የመግቢያ ናሙናዎች

የመግቢያ ናሙናዎች

ንቁ!

ንቁ! ቁጥር 3 2017 | መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል ነው?

ጥያቄ፦ መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል እንደሆነ ይሰማሃል? ወይስ የሰዎችን ሐሳብ የያዘ መጽሐፍ?

ጥቅስ፦ 2ጢሞ 3:16

አበርክት፦ ይህ የንቁ! እትም መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የአምላክ ቃል መሆኑን የሚያሳዩ ሦስት አሳማኝ ማስረጃዎችን ያብራራል።

እውነትን አስተምሩ

ተገልጦ የተቀመጠ መጽሐፍ ቅዱስ

ጥያቄ፦ ስጦታ ለሆነው ሕይወታችን ምን አመለካከት ሊኖረን ይገባል?

ጥቅስ፦ ራእይ 4:11

እውነት፦ ሕይወት ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ በመሆኑ ለሕይወታችን አክብሮት እንዳለን ልናሳይ ይገባል። ጉዳት እንዳይደርስብን ጥንቃቄ እናደርጋለን፤ እንዲሁም የሌላን ሰው ሕይወት ሆን ብለን አናጠፋም። ሕይወታችንን እንደ ውድ ነገር አድርገን እንመለከተዋለን።

የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው? (T-32)

የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው?

ጥያቄ፦ በዚህ ትራክት የፊት ገጽ ላይ የቀረበውን ጥያቄና ከታች ያሉትን መልስ ሊሆኑ የሚችሉ ሐሳቦች ተመልከት። አንተ ለዚህ ጥያቄ ምን መልስ ትሰጣለህ?

ጥቅስ፦ ሉቃስ 11:28

አበርክት፦ ይህ ጥቅስ ቤተሰብህን እንዴት ሊጠቅም እንደሚችል እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ነገር ላይ እምነት መጣል የምንችለው ለምን እንደሆነ በዚህ ትራክት ላይ ተብራርቷል።

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።