በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውጤታማ ደብዳቤ መጻፍ

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ውጤታማ ደብዳቤ መጻፍ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሐዋርያው ጳውሎስ የእምነት አጋሮቹን ለማበረታታት ከጻፋቸው 14 ደብዳቤዎች አንዱ 1 ቆሮንቶስ ነው። ደብዳቤ በምንጽፍበት ጊዜ፣ በሚገባ የታሰበባቸውን ቃላት መርጠን ለመጠቀም አጋጣሚ ይኖረናል፤ ተቀባዩም ቢሆን ደብዳቤውን ደጋግሞ ማንበብ ይችላል። ደብዳቤ ለዘመዶቻችንና ለሌሎች የምናውቃቸው ሰዎች ለመመሥከር የሚያስችል ጥሩ ዘዴ ነው። በተጨማሪም በአካል አግኝተን ልናነጋግራቸው ላልቻልናቸው ሰዎች ምሥራቹን ለማካፈል የሚያስችል ውጤታማ መንገድ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ምሥራቹ ሲነገረው ፍላጎት ያሳየ አንድ ሰውን በድጋሚ ቤቱ ለማግኘት ተቸግረን ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ በክልላችን ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ሰዎች የሚኖሩት ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግባቸው ሕንፃዎች፣ በቀላሉ መግባት በማይቻልባቸው ግቢዎች አሊያም ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ሊሆን ይችላል፤ በዚህም ምክንያት ሰዎቹን ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል። ታዲያ ለሌሎች በተለይም ለማናውቃቸው ሰዎች ደብዳቤ ስንጽፍ የትኞቹን ነገሮች ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል?

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ግለሰቡን በአካል ብታገኘው ኖሮ የምትነግረውን ነገር በደብዳቤህ ላይ አስፍር። በደብዳቤው መጀመሪያ ላይ ራስህን አስተዋውቅ፤ እንዲሁም የደብዳቤህን ዓላማ በግልጽ ተናገር። ከዚያም የግለሰቡን ትኩረት የሚስብ አንድ ጥያቄ ካነሳህ በኋላ ድረ ገጻችንን እንዲመለከት ልትጋብዘው ትችላለህ። ሰዎችን በቤታቸው መጽሐፍ ቅዱስ ስለምናስጠናበት ዝግጅት ንገረው፤ በተጨማሪም በማስጠኛ ጽሑፎቻችን ላይ የሚገኙ አንዳንድ ምዕራፎችን ጥቀስለት። ከደብዳቤው ጋር መጋበዣ፣ ትራክት አሊያም የአድራሻ ካርድ መላክ ትችላለህ

  • ደብዳቤህ እጥር ምጥን ያለ ይሁን። ግለሰቡ እንዳይሰለቸው ደብዳቤውን አታስረዝመው።​—የናሙና ደብዳቤውን ተመልከት

  • ደብዳቤህ ስህተት እንዳይኖረው ደግመህ አንብበው፤ በተጨማሪም ለማንበብ የማያስቸግር፣ ወዳጃዊ ስሜት የሚንጸባረቅበት፣ አንባቢውን ቅር የማያሰኝ እንዲሁም አዎንታዊ መልእክት የያዘ መሆኑን አረጋግጥ።