ክርስቲያናዊ ሕይወት
ቀላል ሕይወት መምራታችን አምላክን ለማወደስ ረድቶናል
በአሁኑ ጊዜ፣ በቀላሉ ሕይወታችን በተለያዩ ነገሮች ሊጠላለፍ ይችላል። አንድን ነገር ለመግዛት፣ ክፍያ ለመፈጸም፣ ለመጠቀም፣ ለመጠገን እንዲሁም ለመንከባከብ ጊዜና ጉልበት ያስፈልጋል። ኢየሱስ ቀላል ሕይወት ይመራ ነበር፤ ይህም ቁሳዊ ነገሮች ትኩረቱን እንዳይከፋፍሉትና አገልግሎቱን ከመፈጸም እንዳይዘናጋ አድርጎታል።—ማቴ 8:20
በአገልግሎት ይበልጥ ለመካፈል አኗኗርህን ቀላል ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው? ቢያንስ አንደኛው የቤተሰባችሁ አባል አቅኚ እንዲሆን አንዳንድ ማስተካከያዎችን ማድረግ ትችሉ ይሆን? አሁን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ብትሆኑም ቁሳዊ ነገሮች ቀስ በቀስ ሕይወታችሁን እያወሳሰቡት ይሆን? ቀላል ሕይወት በመምራት ይሖዋን ማገልገል ደስተኛና እርካታ ያለው ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋል።—1ጢሞ 6:7-9
ሕይወትህን ቀላል ማድረግ የምትችልባቸውን መንገዶች ጻፍ።