በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 30

አባቴ፣ አምላኬና ወዳጄ

አባቴ፣ አምላኬና ወዳጄ

(ዕብራውያን 6:10)

  1. 1. ችግር፣ መከራ ሞልቶት

    ሕይወት ከባድ ቢሆንብኝም፣

    መኖሬ ዋጋ ’ንዳለው

    አልጠራጠርም።

    (አዝማች)

    ጻድቅ የሆነው አምላክ

    መቼም ቢሆን ፍቅሬን አይረሳም።

    ብቻዬን አይደለሁም፤

    ካጠገቤ አለ ሁሌም።

    እሱ ጠባቂዬ ነው፤

    ይንከባከበኛል ምንጊዜም።

    አባቴና አምላኬ ነው፤

    ወዳጄም ነው።

  2. 2. ወጣትነቴ አልፎ፣

    የጭንቀት ዘመን መጥቶብኛል።

    ቢሆንም በ’ምነት ዓይኔ

    ተስፋው ይታየኛል።

    (አዝማች)

    ጻድቅ የሆነው አምላክ

    መቼም ቢሆን ፍቅሬን አይረሳም።

    ብቻዬን አይደለሁም፤

    ካጠገቤ አለ ሁሌም።

    እሱ ጠባቂዬ ነው፤

    ይንከባከበኛል ምንጊዜም።

    አባቴና አምላኬ ነው፤

    ወዳጄም ነው።

(በተጨማሪም መዝ. 71:17, 18⁠ን ተመልከት።)