በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“በሕይወታችን እንደ ሠርጋችን ቀን ደስ ብሎን አያውቅም”

“በሕይወታችን እንደ ሠርጋችን ቀን ደስ ብሎን አያውቅም”

“በሕይወታችን እንደ ሠርጋችን ቀን ደስ ብሎን አያውቅም”

የሠርግ ቀን በጣም አስደሳች ወቅት ነው። ብዙ ባለ ትዳሮች “በሕይወታችን እንደ ሠርጋችን ቀን ደስ ብሎን አያውቅም” ብለዋል። ይሁን እንጂ የሠርግ ቀን የማይረሳ የችግር ቀን ሆኖ የሚያልፍበት ጊዜም አለ። በርካታ ውሳኔዎችንና ዝግጅቶችን የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ ሙሽራውና ሙሽራይቱ በርካታ ሰዎችን ተቀብለው ለማስተናገድ ስለሚገደዱ በሙሽሮቹና በቤተሰቦቻቸው ላይ የሚደርሰው ውጥረትና ጫና በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።

የሠርግ ቀን ለተጋቢዎቹ አዲስ የሕይወት ዘመን መጀመሪያ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ለውጥ የሚነካው ተጋቢዎቹን ብቻ አይደለም። ሴት ልጅ ወይም ወንድ ልጅ፣ እህት ወይም ወንድም ሲያገባ አንድ የሚወዱት ሰው አዲስ ጎጆ መመስረቱ ስለሚሆን በቤተሰቡ ላይ የተደባለቀ ስሜት ማስከተሉ አይቀርም።

ጋብቻ የሚካሄድበት ሥርዓት ከአገር አገር ስለሚለያይ ሁሉንም በዝርዝር ማቅረብ አይቻልም። ይህ ጽሑፍ የሚያተኩረው በምዕራባውያንና ከምዕራባውያን አገሮች ጋር ተመሳሳይ ባሕል ባላቸው አገሮች በተለመዱት የጋብቻ ልማዶች ላይ ነው። በእነዚህ አገሮች ጋብቻ ከፍተኛ ወጪ ሊጠይቅ ይችላል። አንዳንዶች ለሠርጋቸው አዳራሽ ወይም ምግብ ቤት በመከራየትና ድግስ በማዘጋጀት በቀላሉ የማይገመት ገንዘብ ያወጣሉ። በኢጣሊያ አንድ መካከለኛ ነው የሚባል ሠርግ 85, 000 ብር ያህል እንደሚያስወጣ ይገመታል። በጃፓንና በሌሎች አገሮች ወጪው ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ ወጪውን የሚሸፍኑት ሙሽሮቹ ሳይሆኑ የሙሽሮቹ ወላጆች ናቸው።

የሠርግ ዝግጅት ከፍተኛ ትርፍ የሚያስገኝ ንግድ ሆኗል። ብዙ የንግድ ድርጅቶች ምንም የማይጎድለው “የተዋጣለት” ሠርግ መደገስን ያደፋፍራሉ። “ሠርግና ሞት አንድ ጊዜ ነው!” ይላሉ። ስለዚህ ይህን ሁለተኛ የማይደገም ቀን “የተዋጣለት” ለማድረግ “አስፈላጊ” ናቸው የሚባሉ በርካታ ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ለሽያጭ ያቀርባሉ። በልዩ ትእዛዝ የሚዘጋጁ የግብዣ ወረቀቶች፣ ታይቶ የማያውቅ የሙሽራ ልብስ፣ የሚዜዎች ልብስ፣ የወንድ ሚዜዎችና የአጃቢዎች ሙሉ ልብሶች ይኖራሉ። በተጨማሪ ደግሞ አበባዎች፣ ሊሞዚን መኪናዎች፣ ግብዣ የሚደረግበት አዳራሽ፣ ፎቶግራፍ አንሺ፣ የሙዚቃ ባንድና ሌሎች ነገሮች ይኖራሉ። ሙሽራይቱና ሙሽራው የሚፈልጓቸው እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ሌሎች ወጪዎች ለወላጆች ራስ ምታት ሊሆኑ ይችላሉ።

በተለያዩ ማኅበረሰቦች ለባሕል ትልቅ ግምት ይሰጣል። እያንዳንዱ የሥርዓቱ ክፍል ተግባራዊ መሆን አለበት ተብሎ ስለሚታሰብ ሙሽራይቱና ሙሽራው እነዚህን ነገሮች አሟልተው እንዲገኙ ይጠበቅባቸዋል። አዎን፣ መሟላት የሚኖርባቸው ነገሮች በጣም በርካታ ሲሆኑ እነዚህን ለማደራጀት የሚኖረው ጊዜ ግን በጣም አጭር ሊሆን ይችላል።

ይህ ሁሉ ገና ከሩቁ ያስፈራሃል ወይስ ያጓጓሃል? መልስህ ምንም ይሁን ምን የሠርግ ቀን ስለሚጠይቃቸው ነገሮች ማሰብ በርካታ ጥያቄዎች ያስነሳል። ባሁኑ ጊዜ ለጋብቻ የሚሰጠው ትርጉም ምንድን ነው? “ትክክለኛ” በሚባለው መንገድ ለመጋባት ይህ ሁሉ ሽርጉድ ያስፈልጋል? በሠርግ ዝግጅት ምክንያት የሚነሱትን ተግባራዊና ስሜታዊ ችግሮች እንዴት መቋቋም ይቻላል?

የሠርግ ቀን ከፍተኛ ጫና የሚያስከትል ቢሆንም የተሳካና አስደሳች ሠርግ ለማዘጋጀት የቻሉ በርካታ ሰዎች አሉ። የእነዚህ ሰዎች ተሞክሮ ለሠርግ በመዘጋጀት ላይ ያሉትን ሊረዳ ይችል ይሆናል። በተጨማሪም የሠርጉ ቀን ማራኪ፣ አስደሳችና ሁሉንም የሚያንጽ መሆን ይችል ዘንድ የሠርግ ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜ እርዳታ ሊሰጡ የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች አሉ።