በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከዓመፀኝነት ለመላቀቅ የሚያስችል እርዳታ

ከዓመፀኝነት ለመላቀቅ የሚያስችል እርዳታ

ከዓመፀኝነት ለመላቀቅ የሚያስችል እርዳታ

በፈረንሳይ የሚገኝ የንቁ! መጽሔት ዘጋቢ እንዳጠናቀረው

በፈረንሳይ ከተሞች ውስጥ በሚገኙ ቸል በተባሉ በርካታ አካባቢዎች የሕግና ሥርዓት መጣስ አሳሳቢ እየሆነ እንደመጣ በቅርብ የተከሰቱ ሁኔታዎች ይፋ አድርገዋል። በፈረንሳይኛ የሚዘጋጅ ሌክስፕሬስ የተባለ መጽሔት “በከተማ የሚፈጸመው ዓመፅ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አምስት እጥፍ ገደማ ጨምሯል” ሲል ዘግቧል። ከዚህም በላይ አሰቃቂ ወንጀል የሚፈጽሙ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ መጥቷል።

ወጣት ጥፋተኞች በሥርዓት አልበኝነት፣ በዕፅ አዘዋዋሪነት፣ በንጥቂያ፣ በቤት ማቃጠል ወንጀልና በስርቆት ከመካፈላቸው በተጨማሪ የመንግሥት ተወካዮችን የጥቃት ዒላማቸው አድርገዋል። ዘወትር የጥቃት ሰለባ ከሚሆኑት መካከል ፖሊሶች፣ የእሳት አደጋ መከላከያና የሕዝብ ትራንስፖርት ሠራተኞች ይገኙበታል።

ዓመፅ ይህን ያክል የበዛው ለምንድን ነው? ሁለት የማኅበራዊ ኑሮ ጠበብት “በማንኛውም ሥልጣን ላይ ለሚፈጸመው ዓመፅ መንስዔው የቤተሰብ መፈራረስ ነው” በማለት ተናግረዋል። በተጨማሪም “[ወጣቶቹ] በባለሥልጣናት ቸል እንደተባሉ ስለሚሰማቸውና” ምንም “ብሩህ ተስፋ” ስለማይታያቸው ይህን ዓመፅ ለመፈጸም እንደሚነሳሱ ጠቅሰዋል።

የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ የያዘውን ተስፋ ዓመፅ በበዛባቸው አካባቢዎችም ዘወትር ይሰብካሉ። አንድ ጋዜጠኛ በፈረንሳይ ቴሌቪዥን በቅርቡ በተላለፈ ፕሮግራም ላይ እንደሚከተለው ሲል ተናግሯል:- “የይሖዋ ምሥክሮች የማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ፖሊሶችና መንግሥት ችላ ባሏቸው የከተማ ዳርቻዎችና የተረሱ መንደሮች ውስጥ እንኳን ሳይቀር ይገባሉ። በእነዚህ ሕንፃዎችና ጎዳናዎች ላይ ይናገራሉ እንዲሁም ያዳምጣሉ።” ንቁ! መጽሔትን ከሚያነብ ከአንድ ወጣት የተላከው የሚከተለው ደብዳቤ ሥራቸው በጎ ተጽዕኖ እንዳሳደረ ያሳያል።

“እነዚህን ጽሑፎች ስለምታዘጋጁ ከልብ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ። እኔን በግል ከመርዳት ባሻገር ከወላጆቼ ጋር ያለኝን ግንኙነት እንዳሻሽል አድርጋችሁኛል። የ16 ዓመት ወጣትና የእስልምና እምነት ተከታይ ነኝ።

“ከዓመፀኝነት እንድላቀቅ ማድረግ የቻላችሁ መሆኑን ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። በዚህ ምክንያት ሃይማኖቴን ይበልጥ መከታተል ችያለሁ፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስንም አነብባለሁ። ምስጋና ይድረሳችሁና ትምህርቴንም ቀጥያለሁ። ከዚህም በተጨማሪ በመንደራችን የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች መጽሔቶቻችሁን በየወሩ ከእኔ ተውሰው ስለሚያነቡ ከዓመፀኝነት መላቀቅ ችለዋል። ትልቅ ውለታ ስለዋላችሁልኝ በጣም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።”