መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ኅዳር 2017

ይህ እትም ከታኅሣሥ 25, 2017 እስከ ጥር 28, 2018 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

በደስታ ዘምሩ!

በጉባኤ ውስጥ መዘመር የሚያሳፍርህ ከሆነ ይህን ስሜት አሸንፈህ ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር መዘመር እንድትችል ምን ይረዳሃል?

ይሖዋን መጠጊያችሁ አድርጋችሁታል?

በጥንቷ እስራኤል የነበረው የመማጸኛ ከተሞች ዝግጅት አምላክ ይቅር ባይ መሆኑን ያስተምረናል።

ፍትሕና ምሕረት በማሳየት ይሖዋን ምሰሉ

የመማጸኛ ከተሞች ዝግጅት ይሖዋ መሐሪ አምላክ መሆኑን የሚያሳየው እንዴት ነው? ይሖዋ ለሕይወት ስላለው አመለካከት ምን ያስተምረናል? ይህ ዝግጅት የይሖዋ ፍትሕ ፍጹም እንደሆነ የሚያሳየው እንዴት ነው?

“ለጋስ ሰው ይባረካል”

ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና ያሉንን ሌሎች ነገሮች ተጠቅመን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ መደገፍ እችላለን።

ከዓለማዊ አስተሳሰብ ራቁ

በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ አስተሳሰቦች ተጽዕኖ እንዳያሳድሩብን ለመከላከል ሁላችንም ጥረት ማድረግ አለብን። ዓለማዊ አስተሳሰብን የሚያንጸባርቁ አምስት ሐሳቦችን እንመልከት።

ማንኛውም ነገር ሽልማቱን እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ

ጳውሎስ፣ የእምነት ባልንጀሮቹን ከፊታቸው ስለተዘረጋው አስደናቂ ተስፋ ካስታወሳቸው በኋላ ፍቅር የተንጸባረቀበት ማሳሰቢያ ሰጥቷቸዋል።

ከአዲሱ ጉባኤህ ጋር መላመድ የምትችለው እንዴት ነው?

አንተም ወደ ሌላ ጉባኤ ተዛውረህ ከሆነ በተወሰነ ደረጃ ስጋት አድሮብህ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ከጉባኤው ጋር ለመላመድ ምን ሊረዳህ ይችላል?