ልጆቻችሁን አስተምሩ

ወላጆች፣ በእነዚህ ታሪኮች ተጠቅማችሁ ልጆቻችሁን ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት አስተምሯቸው።

መግቢያ

በዘዳግም መጽሐፍ ላይ ያለው ሐሳብ ልጆቻችሁን ስታሳድጉ መመሪያ ሊሆናችሁ ይችላል።

ትምህርት 1

አስደሳች የሆነ ሚስጥር

መጽሐፍ ቅዱስ ልዩ ስለሆነ አንድ ሚስጥር ይናገራል፤ ይህን ሚስጥር “ቅዱስ ሚስጥር” በማለት ይጠራዋል። ይህ ሚስጥር ምን እንደሆነ ለማወቅ ትፈልጋለህ?

ትምህርት 2

ርብቃ ይሖዋን ማስደሰት ትፈልግ ነበር

እኛስ እንደ ርብቃ ለመሆን ምን ማድረግ እንችላለን? ታሪኳን በማንበብ ስለ እሷ ይበልጥ እንድታውቅ እንጋብዝሃለን።

ትምህርት 3

ረዓብ በይሖዋ ላይ እምነት ነበራት

ኢያሪኮ ስትጠፋ ረዓብና ቤተሰቧ የተረፉት እንዴት እንደሆነ አንብብ።

ትምህርት 4

አባቷንና ይሖዋን አስደስታለች

የዮፍታሔ ልጅ አባቷ የገባውን የትኛውን ቃል ፈጽማለች? እኛስ እሷን መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 5

ሳሙኤል ሁልጊዜ ትክክል የሆነውን ያደርግ ነበር

ሌሎች ሰዎች መጥፎ ነገር በሚያደርጉበት ጊዜም እንኳ ልክ እንደ ሳሙኤል ትክክለኛውን ነገር ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

ትምህርት 6

ዳዊት አልፈራም

ዳዊት ይህን ያህል ደፋር እንዲሆን የረዳው ምን እንደሆነ ለማወቅ ይህንን አስደሳች የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አንብብ።

ትምህርት 7

ብቸኝነትና ፍርሃት ተሰምቶህ ያውቃል?

ኤልያስ ብቻውን እንደሆነ በተሰማው ጊዜ ይሖዋ ምን አለው? ኤልያስ ካጋጠመው ነገር ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?

ትምህርት 8

ኢዮስያስ ጥሩ ጓደኞች ነበሩት

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኢዮስያስ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረግ ከባድ ሆኖበት እንደነበር ይናገራል። ትክክል የሆነውን በማድረግ ረገድ ጓደኞቹ እንዴት እንደረዱት አንብብ።

ትምህርት 9

ኤርምያስ ስለ ይሖዋ መናገሩን አላቆመም

ኤርምያስ ስለ ይሖዋ በመናገሩ ሰዎች ያሾፉበትና የተናደዱበት ቢሆንም ስለ አምላክ መናገሩን ያላቆመው ለምንድን ነው?

ትምህርት 10

ኢየሱስ ምንጊዜም ታዛዥ ነበር

ወላጆችህን መታዘዝ ቀላል የማይሆንበት ጊዜ አለ። በዚህ ረገድ የኢየሱስ ምሳሌ ሊረዳህ የሚችለው እንዴት እንደሆነ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

ትምህርት 11

ስለ ኢየሱስ የጻፉ ሰዎች

መጽሐፍ ቅዱስን ስለ ጻፉ ስምንት ሰዎች እንድታነብ እንጋብዝሃለን፤ እነዚህ ሰዎች ኢየሱስ በኖረበት ዘመን የነበሩ ሲሆኑ ስለ እሱ ሕይወት ጽፈዋል።

ትምህርት 12

ደፋር የሆነው የጳውሎስ እህት ልጅ

ይህ ወጣት የአጎቱን ሕይወት አትርፏል። ይህን ያደረገው እንዴት እንደሆነ ታውቃለህ?

ትምህርት 13

ጢሞቴዎስ ሰዎችን ለመርዳት ይፈልግ ነበር

ሕይወትህ ልክ እንደ ጢሞቴዎስ በጣም አስደሳች እንዲሆን ምን ማድረግ ትችላለህ?

ትምህርት 14

መላዋን ምድር የሚገዛ መንግሥት

ኢየሱስ ምድርን በሚገዛበት ወቅት ምን ዓይነት ሁኔታ ይኖራል? አንተስ በዚያ መገኘት ትፈልጋለህ?