የኢየሱስ ወንጌል

ቀልብ በሚስበው በዚህ ተከታታይ ቪዲዮ አማካኝነት የአምላክ ልጅና የሰው ልጆች አዳኝ ስለሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ይበልጥ እንድታውቅ እንጋብዝሃለን።

የኢየሱስ ወንጌል—አጠቃላይ ይዘት

ወንጌሎች ቀልብ በሚስብ መንገድ የተተረኩበት ተከታታይ የኢየሱስ ድራማ እነሆ!

ክፍል 1፦ እውነተኛው የዓለም ብርሃን

የሰው ዘር በአዳም ምክንያት ከተሸጠበት የኃጢአት ባርነት ነፃ የሚወጣው እንዴት ነው? የሰው ልጆች ብቸኛ ተስፋ መሲሑ ነው።

ክፍል 2፦ “ልጄ ይህ ነው”

መጥምቁ ዮሐንስ ለመሲሑ መንገድ አዘጋጅቷል። ኢየሱስ ምድራዊ አገልግሎቱን እንደጀመረ ያከናወናቸውን አስደናቂ ክንውኖች ተመልከት!

ክፍል 3፦ ‘እኔ እሱ ነኝ’

ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ፣ ለሳምራዊቷ ሴት እንዲሁም ለናዝሬት ነዋሪዎች መሲሕ እንደሆነ ነግሯቸዋል፤ ሆኖም የተቀበሉት ቅን ልቦና ያላቸው ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። አንድ አስደናቂ ተአምር ከፈጸመ በኋላ ትሑት የሆኑ ዓሣ አጥማጆችን ተከታዮቹ እንዲሆኑ ጋበዛቸው።

ክፍል 4፦ “የመጣሁት ለዚሁ ነው”

ኢየሱስ ኃይሉን ተጠቅሞ ሰዎችን ፈወሰ እንዲሁም አጋንንትን አስወጣ። አንዳንዶች ግን የሚያከናውነውን ሥራ የተቃወሙ ሲሆን ሊገድሉት አሴሩ። ኢየሱስ እጅግ ሩኅሩኅ ከመሆኑም ሌላ የተዋጣለት አስተማሪ ስለሆነ ደቀ መዛሙርት አፈራ፤ እንዲሁም 12ቱን ሐዋርያት ሾመ።

ክፍል 5፦ “በትምህርት አሰጣጡ እጅግ ተደነቁ”

ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ከፈወሰ በኋላ በዘመኑ ከነበሩት አስተማሪዎች ሁሉ በላቀ መንገድ ሕዝቡን አስተማረ። እንደ ባለሥልጣን በማስተማሩ፣ በምሳሌዎቹ እንዲሁም ለዕለት ተዕለት ሕይወት የሚጠቅም ትምህርት በመስጠቱ ሕዝቡ እጅግ ተደነቁ።

ክፍል 6፦ “ይመጣል የተባልከው አንተ ነህ?”

ኢየሱስ የሞተ ሰው በማስነሳት ኃይሉን ገለጠ። የፈጸማቸው ተአምራትና ማስተዋል የታከለባቸው ትምህርቶቹ የአድማጮቹን የልብ ዝንባሌ በግልጽ አሳይተዋል። ኢየሱስ ምሳሌዎችን በመጠቀም የመንግሥቱን የተለያዩ ገጽታዎች አብራራ።

የኢየሱስ ወንጌል—የቪዲዮዎቹ ማስተዋወቂያ

የወንጌል ዘገባዎች ሕያው እንዲሆኑልህ የሚያደርጉትን ተከታታይ ቪዲዮዎች ማስተዋወቂያ ተመልከት።