የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ነሐሴ 2018
የውይይት ናሙናዎች
መጽሐፍ ቅዱስ ለዘመናችንም ጠቃሚ ምክር የያዘ መጽሐፍ ስለመሆኑ ለመወያየት የሚረዱ የውይይት ናሙናዎች።
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
አመስጋኝ ሁኑ
ክርስቶስን ማስደሰት የሚፈልጉ ሰዎች ብሔር፣ ዘር ወይም ሃይማኖት ሳይለዩ ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ፍቅር የማሳየትና አመስጋኝነታቸውን የመግለጽ ግዴታ አለባቸው።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
የሎጥን ሚስት አስታውሱ
እንደ ሎጥ ሚስት የአምላክን ሞገስ እንዳናጣ ምን ሊረዳን ይችላል? በሕይወታችን ውስጥ ለቁሳዊ ነገሮች የምንሰጠው ቦታ ለመንፈሳዊ ነገሮች የምንሰጠውን ቦታ እየተሻማብን እንደሆነ ካስተዋልን ምን ማድረግ ይኖርብናል?
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ከአሥሩ ምናን ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?
ኢየሱስ ስለ አሥሩ ምናን በተናገረው ምሳሌ ላይ መስፍኑ፣ ባሪያዎቹና ገንዘቡ ምን ያመለክታሉ?
ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—JW.ORGን መጠቀም
ለማስተማር በምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች ውስጥ የተካተቱት የሕትመት ውጤቶች በሙሉ ወደ jw.org ይመራሉ። ድረ ገጹን በሚገባ መጠቀም ከቻልን በአገልግሎታችን ይበልጥ ውጤታማ መሆን እንችላለን።
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
‘መዳናችሁ እየቀረበ ነው’
ኢየሱስ በቅርቡ ክፉዎችን ለማጥፋትና ታማኝ የሆኑትን ለማዳን ይመጣል። መዳናችንን ለማረጋገጥ በመንፈሳዊ ዝግጁ ሆነን መጠበቅ አለብን።
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ይቅር ለማለት ዝግጁ ሁኑ
ይሖዋና ልጁ ኃጢአተኛ ለሆኑ የሰው ልጆች ምሕረት ለማድረግ የሚያስችላቸው መሠረት ለማግኘት ሲሉ ሰዎቹ የልብ ለውጥ ማድረጋቸውን በንቃት ይከታተላሉ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ኢየሱስ ለወንድምህም ጭምር ሞቶለታል
ኢየሱስ ፍጹም ላልሆኑ ሰዎች ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጓል። ልክ እንደ እኛ ፍጹማን ላልሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የክርስቶስን ዓይነት ፍቅር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?