በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

“ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”!

የ2019 የይሖዋ ምሥክሮች የክልል ስብሰባ

የይሖዋ ምሥክሮች ባዘጋጁት የክልል ስብሰባ ላይ እንዲገኙ በአክብሮት ጋብዘንዎታል።

የስብሰባው ጎላ ያሉ ገጽታዎች

  • “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል” የሚለው አገላለጽ ምን ትርጉም እንዳለው ይብራራል። እንዲሁም መጥፎ አስተዳደግ ያለህ፣ ሥር በሰደደ ሕመም የምትሠቃይ ወይም በከባድ ድህነት ውስጥ የምትኖር ቢሆንም ፍቅርህን ማጠናከር የምትችለው እንዴት እንደሆነ የሚያብራሩ ንግግሮች ይቀርባሉ። በተጨማሪም የአምላክ የፍጥረት ሥራዎች የእሱን ፍቅር የሚያንጸባርቁት እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ አጫጭር ጥናታዊ ቪዲዮዎች ይታያሉ።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ባሎች፣ ሚስቶችና ልጆች አንዳቸው ለሌላው የማይከስም ፍቅር ማሳየት እንዲችሉ እየረዷቸው ያሉት እንዴት እንደሆነ ይብራራል።

  • “ጥላቻ በሞላበት ዓለም ውስጥ እውነተኛ ፍቅር የሚገኘው የት ነው?” የሚል ርዕስ ያለው ንግግር በዓለም ዙሪያ ያሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ፍቅርን ማዳበራቸው አድልዎንና ጥላቻን እንዲያስወግዱ የረዳቸው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሰ ኢዮስያስ የተባለ የአምላክ አገልጋይ ሕይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን ፊልም ይታያል። ኢዮስያስ ያደገው ክፉ አድራጊ በሆኑ ሰዎች መካከል ነው። ሆኖም “ታማኝ ፍቅር የተንጸባረቀባቸው ተግባራት” በማከናወን መልካም ስም ማትረፍ ችሏል። (2 ዜና መዋዕል 35:26) የኢዮስያስ ታሪክ፦ ይሖዋን ውደዱ፤ ክፉ የሆነውን ነገር ጥሉ የሚል ርዕስ ያለው ባለ ሁለት ክፍል ፊልም ቅዳሜና እሁድ ላይ ይቀርባል።

  • በአብዛኞቹ የክልል ስብሰባዎች ላይ ከዓለም ዙሪያ የመጡ ልዑካንና ሚስዮናውያን ይገኛሉ። በዚህ ስብሰባ ላይ ፍቅር የዘር፣ የጎሳና የፖለቲካ ልዩነቶችን ማሸነፍ እንደሚችል ማየት ትችላለህ።

መግቢያ በነፃ ነው

ሙዳየ ምጽዋት አይዞርም

የስብሰባውን ፕሮግራም ማየት እንዲሁም ስለ ክልል ስብሰባዎቻችን የሚገልጽ ቪዲዮ መመልከት ይችላሉ።

ለአንተ ቅርብ የሆነውን ቦታ ፈልግ