በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ከቢሮዎቻችንና ከጉብኝት ጋር የተያያዘ መረጃ

ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንንና የሕትመት ሥራችንን እንድትጎበኝ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን። ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ የሚገኙበትን ቦታና የጉብኝት ሰዓቱን ማወቅ ትችላለህ።

ጀርመን

Jehovas Zeugen

Am Steinfels

65618 SELTERS

GERMANY

+49 6483-41-0

የጉብኝት ፕሮግራም

ከሰኞ እስከ ዓርብ

ጠዋት ከ2:00 እስከ 4:00 እና ከሰዓት ከ7:00 እስከ 9:00

በአስጎብኚ የሚከናወነው ጉብኝት 2 ሰዓት ይወስዳል

ታሪካዊ መረጃዎችን ለመጎብኘት ተጨማሪ አንድ ሰዓት ሊያስፈልግ ይችላል

ጎብኚዎቹ ብዙ ከሆኑ አስቀድመው ቢያስመዘግቡ የተሻለ ነው

ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች

በሴልተርስ፣ ጀርመን የሚገኘው የማዕከላዊ አውሮፓ ቅርንጫፍ ቢሮ በኦስትሪያ፣ በጀርመን፣ በሊክተንስታይን፣ ሉክሰምበርግና በስዊዘርላንድ የሚከናወነውን የስብከት ሥራ በበላይነት ይከታተላል። ጉብኝቱ በእነዚህ የማዕከላዊ አውሮፓ አገሮች የሚካሄደው የስብከት ሥራ ያስመዘገበውን ታሪክ ያጠቃልላል። በተጨማሪም ይህ ቅርንጫፍ ቢሮ በ51 አገሮች ውስጥ ለሚገኙ ከ16,000 ለሚበልጡ ጉባኤዎች ጽሑፎችን አትሞ ይልካል።

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ።