9. የዓለም መጨረሻ ቀርቧል?

9. የዓለም መጨረሻ ቀርቧል?

1 ይሖዋ ወደፊት የሚሆነውን ነገር ገልጾልናል

“ከመጀመሪያ መጨረሻውን፣ ገና ያልተከናወኑትንም ነገሮች ከረጅም ጊዜ በፊት አስቀድሜ እናገራለሁ።”—ኢሳይያስ 46:10

የመጨረሻውን ጊዜ በተመለከተ ምን ነገሮችን እናውቃለን?

 • ዳንኤል 7:13, 14

  ኢየሱስ በ1914 በሰማይ ንጉሥ ሆኖ ተሹሟል።

 • ማቴዎስ 24:3-14

  ኢየሱስ፣ የሚያስጨንቅ ጊዜ እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል።

 • ራእይ 12:7-9, 12

  ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ ከተሾመ በኋላ ሰይጣንን ከሰማይ ወደ ምድር ወርውሮታል። አምላክ ሰይጣንን በቅርቡ ያስወግደዋል፤ ሰይጣን “ጥቂት ጊዜ እንደቀረው ስላወቀ” በጣም ተቆጥቷል።

2 የምንኖረው በመጨረሻው ጊዜ ውስጥ ነው

“የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ [ምልክት] ምንድን ነው?”—ማቴዎስ 24:3

የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች እየተፈጸሙ እንደሆነ አስተውለሃል?

 • ማቴዎስ 24:7፤ ሉቃስ 21:11

  ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ዛሬ ስለ ጦርነት፣ ስለ ረሃብ፣ ስለ በሽታና ስለ ምድር ነውጥ መስማት የተለመደ ነገር ሆኗል።

 • 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

  ሐዋርያው ጳውሎስ በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚኖሩ ሰዎች ስለሚያሳዩት ባሕርይ ተናግሯል።

 • ዳንኤል 12:4

  አምላክ፣ አገልጋዮቹ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ መጽሐፍ ቅዱስን መረዳት እንዲችሉ የማስተዋል ችሎታ ሰጥቷቸዋል።

 • ማቴዎስ 24:14

  የአምላክ መንግሥት ምሥራች በዓለም ዙሪያ እየተሰበከ ነው።

3 ይሖዋን ለማስደሰት አሁኑኑ እርምጃ ውሰድ

“የይሖዋ ቀን የሚመጣው ሌባ በሌሊት በሚመጣበት መንገድ [ነው]።”—1 ተሰሎንቄ 5:2

መጨረሻው በጣም እንደቀረበ ማወቅህ ምን እንድታደርግ ሊያነሳሳህ ይገባል?

 • ዮሐንስ 17:3

  መጽሐፍ ቅዱስን በቁም ነገር አጥና።

 • ዕብራውያን 10:24, 25

  የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ስብሰባዎች ላይ በመገኘት ይበልጥ ለመማር ጥረት አድርግ።

 • ያዕቆብ 4:8

  ወደ አምላክ ይበልጥ መቅረብ እንድትችል በሕይወትህ ላይ አንዳንድ ማስተካከያዎች አድርግ።

 • ሉቃስ 21:34-36

  ትኩረትህን የሚከፋፍሉ ነገሮችን አስወግድ፤ ሕይወትህ ለይሖዋ በምታቀርበው አምልኮ ላይ ያተኮረ ይሁን።