8. የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
1 የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛ መስተዳድር ነው
“መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም።”—ማቴዎስ 6:9-13
የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
ራእይ 11:15
የአምላክ መንግሥት ከሰማይ ሆኖ ምድርን የሚገዛ መስተዳድር ነው።
1 ጢሞቴዎስ 6:15
ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ነው።
ራእይ 14:1, 4
መቶ አርባ አራት ሺህ ሰዎች ከኢየሱስ ጋር አብረው በሰማይ ይገዛሉ።
ዕብራውያን 4:15፤ 5:8
ኢየሱስና 144,000ዎቹ ስሜታችንንም ሆነ ያሉብንን ችግሮች ይረዳሉ።
2 ኢየሱስ ተወዳዳሪ የሌለው ገዢ ይሆናል
“ለችግረኞች [ወይም ለድሆች] በትክክል ይፈርዳል።”—ኢሳይያስ 11:4
ኢየሱስ ተወዳዳሪ የሌለው ንጉሥ ይሆናል የምንለው ለምንድን ነው?
1 ጢሞቴዎስ 6:16
ሰብዓዊ ገዢዎች የተወሰነ ዕድሜ ኖረው መሞታቸው አይቀርም፤ ኢየሱስ ግን ፈጽሞ አይሞትም። ኢየሱስ የሚያደርግልን መልካም ነገሮች በሙሉ ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኙ ናቸው።
ኢሳይያስ 11:2-4
ኢየሱስ ከየትኛውም ሰብዓዊ ገዢ ይበልጥ መልካም ነገር ማድረግ ይችላል። ሰብዓዊ ገዢዎች አንድ ላይ ቢተባበሩ እንኳ የኢየሱስን ያህል ኃይል ሊኖራቸው አይችልም። ኢየሱስ ፍትሐዊና ሩኅሩኅ ነው።
3 የአምላክ መንግሥት የይሖዋ ፈቃድ እንዲፈጸም ያደርጋል
“የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል።”—ዳንኤል 2:44
የአምላክ መንግሥት እስካሁን ምን ነገሮችን አድርጓል? ወደፊትስ ምን ያደርጋል?
ራእይ 12:7-12
ኢየሱስ በ1914 ንጉሥ ሆኖ ከተሾመ በኋላ ሰይጣንን ከሰማይ ወደ ምድር ወርውሮታል። በምድር ላይ ችግር፣ ሥቃይና መከራ የበዛው ለዚህ ነው።
መክብብ 8:9፤ ራእይ 16:16
በአርማጌዶን ጦርነት ወቅት የአምላክ መንግሥት ጨካኝና ምግባረ ብልሹ የሆኑ ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ ያስወግዳል።
መዝሙር 37:10
ክፉዎች ይጠፋሉ።
ራእይ 22:1-3
የአምላክ መንግሥት ምድርን በሚገዛበት ጊዜ የሚታመምም ሆነ የሚሞት ሰው አይኖርም፤ የሰው ልጆች በሙሉ የአምላክን ስም ያከብራሉ።