3. አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
1 አምላክ እኛን የፈጠረው በዓላማ ነው
“ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”—መዝሙር 37:29
አምላክ ለሰዎች ያለው ዓላማ ምንድን ነው?
ዘፍጥረት 1:28
የአምላክ ዓላማ የሰው ልጆች ምድርን ገነት እንዲያደርጉና እንስሳትን እንዲንከባከቡ ነበር።
ኢሳይያስ 46:9-11፤ 55:11
አምላክ ዓላማውን ይፈጽማል፤ ደግሞም እንዲህ እንዳያደርግ ሊከለክለው የሚችል ምንም ነገር የለም።
2 ሕይወት በመከራ የተሞላው ለምንድን ነው?
“መላው ዓለም . . . በክፉው ቁጥጥር ሥር ነው።”—1 ዮሐንስ 5:19
ዓለምን የሚገዛው ማን ነው?
ዮሐንስ 12:31
ኢየሱስ የዚህ ዓለም ገዢ ሰይጣን እንደሆነ ተናግሯል።
ያዕቆብ 1:13-15
ሰይጣን የራሱ ያልሆነውን ነገር ተመኝቷል።
ዘፍጥረት 2:17፤ 3:1-6
ሰይጣን ሔዋንን አታለላት፤ አዳምና ሔዋን አምላክን ባለመታዘዛቸው ከጊዜ በኋላ ሞቱ።
ሮም 3:23፤ 5:12
ከአዳም ኃጢአት ስለወረስን እኛም እንሞታለን።
2 ቆሮንቶስ 4:3, 4
ሰይጣን ሰዎችን ያሳስታል።
3 የአምላክ መንግሥት መፍትሔ ይሰጣል
“መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ . . . በምድርም ላይ ይፈጸም።”—ማቴዎስ 6:10
ይሖዋ ወደፊት ምን ያደርጋል?
ዳንኤል 2:44
አምላክ ያቋቋመው መስተዳድር የዓለምን መንግሥታት ሁሉ አጥፍቶ ብቻውን ይገዛል።
ራእይ 16:14-16
አምላክ በክፋት የተሞላውን ይህን ዓለም በአርማጌዶን ጦርነት ያጠፋዋል።
ኢሳይያስ 9:6, 7
ይሖዋ ኢየሱስን በሰማይ ያለው መስተዳድር ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። ኢየሱስ ምድርን ይገዛል።
4 የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋታል
“አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታሟላለህ።”—መዝሙር 145:16
የአምላክ መንግሥት ምን ነገሮችን ያደርግልናል?
መዝሙር 46:9
ጦርነት፣ ወንጀልና ዓመፅ ይወገዳል።
ኢሳይያስ 32:18፤ 65:21-24
በአዲሱ ዓለም ውስጥ ሰዎች ሁሉ የሚያማምሩ ቤቶችና የአትክልት ቦታዎች ይኖሯቸዋል፤ በዚያም ተስማምተው በሰላም ይኖራሉ።
መዝሙር 72:16
የተትረፈረፈ ምግብ ይኖራል።
ኢሳይያስ 11:6-9
ሰዎችና እንስሳት በሰላም ይኖራሉ።
ኢሳይያስ 33:24፤ የሐዋርያት ሥራ 24:15
የሚታመም ሰው አይኖርም፤ የሞቱ ሰዎች ይነሳሉ።