2. መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ

2. መጽሐፍ ቅዱስ—ከአምላክ ያገኘነው ስጦታ

1 መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው

“ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው።”—2 ጢሞቴዎስ 3:16

መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች መጻሕፍት የተለየ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ከሁለት ሺህ ስምንት መቶ በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች የተተረጎመ ሲሆን በቢሊዮን በሚቆጠሩ ቅጂዎች ታትሟል።

ከየትም ልናገኘው የማንችለውን እውቀት ይሰጠናል።

 • 1 ተሰሎንቄ 2:13

  የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት አምላክ ነው።

 • 2 ጴጥሮስ 1:21

  አምላክ ሐሳቡን ለማስተላለፍ በሰዎች ተጠቅሟል።

2 መጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶችን የያዘ መጽሐፍ ነው

‘አምላክ ሊዋሽ አይችልም።’—ቲቶ 1:2

በመጽሐፍ ቅዱስ መተማመን የምትችለው ለምንድን ነው?

 • ኢሳይያስ 44:27–45:2

  መጽሐፍ ቅዱስ ባቢሎን ድል እንደምትደረግ ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት ትንቢት ተናግሮ ነበር።

 • 2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

  በዛሬው ጊዜ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች እየተፈጸሙ ነው።

 • ዘኁልቁ 23:19

  መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚናገራቸው ትንቢቶች መፈጸማቸው እንደማይቀር እርግጠኛ መሆን እንችላለን።

3 መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው አንተን ለመርዳት ነው

“የሚጠቅምህን ነገር የማስተምርህ . . . እኔ ይሖዋ አምላክህ ነኝ።”—ኢሳይያስ 48:17

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ትምህርት አገኘህ?

 • ኢዮብ 26:7፤ ኢሳይያስ 40:22

  መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ አንጻር የሚናገረው ነገር ትክክል ነው።

 • ዘኁልቁ 20:2-12

  የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ሁሉንም ነገር በሐቀኝነት ጽፈዋል።

 • ማቴዎስ 5-7

  ኢየሱስ ደስተኞች መሆንና ከሌሎች ጋር ተስማምተን መኖር የምንችለው እንዴት እንደሆነ፣ መጸለይ ያለብን እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ለገንዘብ ምን አመለካከት ሊኖረን እንደሚገባ የሚገልጽ ምክር ሰጥቷል።

4 መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወትህን ሊለውጠው ይችላል

“የአምላክ ቃል ሕያውና ኃይለኛ ነው።”—ዕብራውያን 4:12

የአምላክ ቃል ምን ጥቅሞች ያስገኝልሃል?

 • የአምላክን ዓላማ ለመረዳት ያስችልሃል።

 • ማንነትህን በትክክል እንድታውቅ ይረዳሃል።

 • አምላክ ከአንተ የሚፈልገው ነገር ምን እንደሆነ እንድታውቅ ይረዳሃል።

አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ውድ ስጦታ በመመልከት እንድታነበውና እንድታጠናው ይፈልጋል።