19. ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር

19. ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር

1 ይሖዋ ይወድሃል

“አምላክ ዓለምን እጅግ ከመውደዱ የተነሳ በልጁ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ ሲል አንድያ ልጁን ሰጥቷል።”—ዮሐንስ 3:16

አምላክ እንደሚወድህ ያሳየው እንዴት ነው?

 • መዝሙር 91:2

  ይሖዋ መጠጊያችን ነው። ችግር ሲያጋጥመን ይረዳናል።

 • መዝሙር 37:29

  ለወደፊቱ ጊዜ አስደሳች ተስፋ ሰጥቶናል።

 • 1 ጢሞቴዎስ 6:12, 19

  አምላክ ምንም ዓይነት ችግር በሌለበት ዓለም ውስጥ የዘላለም ሕይወት ይሰጠናል። ውብ በሆነች ገነት ውስጥ ሰላም፣ ደስታና የተሟላ ጤንነት አግኝተን እንኖራለን።

2 ይሖዋ እንድትወደው ይፈልጋል

“አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ አእምሮህ ውደድ።”—ማቴዎስ 22:37

ለአምላክ ያለህ ፍቅር ምን እንድታደርግ ያነሳሳሃል?

 • ሉቃስ 17:12-17

  አምላክ ላደረገልህ ነገር በሙሉ አመስጋኝ ሁን።

 • ማቴዎስ 7:16-20

  በየቀኑ የአምላክን ፈቃድ በማድረግ ለእሱ ያለህን ፍቅር አሳይ።

 • 1 ዮሐንስ 5:3

  የአምላክን ትእዛዛት ጠብቅ።

 • 1 ጢሞቴዎስ 6:18

  ለሌሎች መልካም ለማድረግ የተቻለህን ያህል ጥረት አድርግ።

3 ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት አጠናክር

‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ።’—ይሁዳ 21

ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማጠናከር ምን ሊረዳህ ይችላል?

 • 1 ተሰሎንቄ 5:17

  ዘወትር ጸልይ።

 • ማቴዎስ 28:19, 20፤ 2 ጢሞቴዎስ 4:2

  ስለ አምላክ መንግሥት ለሌሎች ለመናገር ጥረት አድርግ።

 • ምሳሌ 2:1-5

  ስለ ይሖዋ መማርህን ቀጥል።

 • ዕብራውያን 10:24, 25

  አዘውትረህ በስብሰባዎች ላይ ተገኝ። ክርስቲያን ወንድሞችህና እህቶችህ ወደ ይሖዋ ይበልጥ እንድትቀርብ ይረዱሃል።