16. አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ

16. አምላክን በትክክለኛው መንገድ ለማምለክ ቁርጥ ውሳኔ አድርግ

1 ከሐሰት አምልኮ ራቅ

“ከመካከላቸው ውጡና ራሳችሁን ለዩ . . . ርኩስ የሆነውንም ነገር አትንኩ።”—2 ቆሮንቶስ 6:17

ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀምና ወደ ሞቱ ሰዎች መጸለይ ስህተት የሆነው ለምንድን ነው?

 • ዘፀአት 20:4, 5፤ 1 ዮሐንስ 5:21

  ይሖዋ ምስሎችን ለአምልኮ እንድንጠቀም አይፈልግም።

 • ዘዳግም 18:10-12

  ከሞቱ ሰዎች ጋር ለመነጋገር የሚሞክሩ ሰዎች የሚነጋገሩት ከአጋንንት ጋር ነው።

2 በአምላክ ፊት ተቀባይነት ያላቸው ሁሉም በዓላት አይደሉም

“በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ምን እንደሆነ ምንጊዜም መርምራችሁ አረጋግጡ።”—ኤፌሶን 5:10

አንድን በዓል ማክበር ይኖርብህ እንደሆነና እንዳልሆነ መወሰን የምትችለው እንዴት ነው?

 • ሕዝቅኤል 44:23፤ 2 ቆሮንቶስ 6:14, 15

  በዓሉ ከጣዖት አምልኮ የመጣ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ ሞክር።

 • ዘፀአት 32:2-10

  በዓላትን የሚያከብሩ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት መልካም ነገር አስበው ቢሆንም በዓሉ አምላክን ላያስደስተው ይችላል።

 • ዳንኤል 3:1-27

  ሰዎችን፣ ሰብዓዊ ድርጅቶችን ወይም ብሔራዊ አርማዎችን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ በዓላትን ማክበር አይኖርብህም።

 • 1 ጢሞቴዎስ 1:18, 19

  የማመዛዘን ችሎታህን ተጠቀም፤ ምንጊዜም በይሖዋ ፊት ጥሩ ሕሊና እንዲኖርህ ጥረት አድርግ።

3 የምታምንበትን ነገር ለሌሎች በአክብሮት አስረዳ

“ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ምንጊዜም በጨው የተቀመመ ያህል ለዛ ያለው ይሁን።”—ቆላስይስ 4:6

እምነትህን ለሌሎች ማስረዳት ያለብህ እንዴት ነው?

 • ማቴዎስ 7:12

  ሌሎች ውሳኔህን እንዲያከብሩልህ እንደምትፈልግ ሁሉ አንተም የእነሱን ውሳኔ አክብር።

 • 2 ጢሞቴዎስ 2:24

  ምንጊዜም ለሌሎች አሳቢነት አሳይ፤ የምታምንበትን ነገር ለሌሎች ስታስረዳ መጨቃጨቅ አይኖርብህም።

 • 1 ጴጥሮስ 3:15

  የምታምንበትን ነገር በገርነትና በአክብሮት አስረዳ።

 • ዕብራውያን 10:24, 25

  በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ ስትገኝ ማበረታቻ የምታገኝ ከመሆኑም ሌላ ስለ እምነትህ ጥያቄ ሲቀርብልህ ምን መልስ መስጠት እንደምትችል ትማራለህ።