በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የቤቴል ጉብኝት

ቤቴል በሚል ስያሜ የሚታወቁትን ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን እንድትጎበኝ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን። በአንዳንዶቹ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ ያለአስጎብኚ የሚታዩ አውደ ርዕዮችም ተዘጋጅተዋል።

ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ጋር በተያያዘ የተሰጠ ማሳሰቢያ፦ በብዙ አገሮች ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን ማስጎብኘት አቁመናል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክህ መጎብኘት ያሰብከውን ቅርንጫፍ ቢሮ አነጋግር።

ዩናይትድ ስቴትስ

የጉብኝት ቀጠሮ ማስያዝ

መሥሪያ ቤታችንን ለመጎብኘት አስቀድመህ ቀጠሮ ማስያዝ ይኖርብሃል? አዎ። መጨናነቅ እንዳይፈጠርና ሁሉም ጎብኚዎች ዘና ብለው እንዲጎበኙ ለማድረግ ሲባል የሚመጡት እንግዶች በሙሉ (በጉብኝት ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሰዎች ብዛት ምንም ያህል ቢሆን) አስቀድመው ቀጠሮ ማስያዛቸው አስፈላጊ ነው።

አስቀድሞ ቀጠሮ ያላስያዘ ሰው መጎብኘት ይችላል? አስቀድመህ ቀጠሮ ካላስያዝክ መሥሪያ ቤታችንን እንድትጎበኝ ዝግጅት ማድረግ አስቸጋሪ ይሆናል። ካለው ቦታ አንጻር በአንድ ቀን ውስጥ ማስተናገድ የምንችለው የተወሰነ ቁጥር ያላቸውን ጎብኚዎች ብቻ ነው።

ለጉብኝቱ ስንት ሰዓት መድረስ ይኖርብሃል? መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከቀጠሮህ ከአንድ ሰዓት በላይ ቀድመህ ባትመጣ ጥሩ ነው።

የጉብኝት ቀጠሮ ማስያዝ የምትችለው እንዴት ነው? በጉብኝት ቡድኑ ውስጥ ያሉት ሰዎች ብዛት 20 የማይሞላ ከሆነ “የጉብኝት ቀጠሮ አስይዝ—ቁጥራቸው 20 የማይሞላ ሰዎች” የሚለውን ጠቅ አድርግ። ካልሆነ ግን “የጉብኝት ቀጠሮ አስይዝ—20 ወይም ከዚያ በላይ ሰዎች” የሚለውን ጠቅ አድርግ።

ያስያዝከውን የጉብኝት ቀጠሮ መቀየር ወይም መሰረዝ ትችላለህ? አዎ። “የጉብኝት ቀጠሮህን ተመልከት ወይም ቀይር” የሚለውን ጠቅ አድርግ።

ለጉብኝት በመረጥከው ቀን ክፍት ቦታ ባይኖርስ? ለውጥ መኖሩን ለማየት አዘውትረህ ድረ ገጹን ተመልከት። የጉብኝት ቀጠሮዎች ሲቀየሩ ወይም ሲሰረዙ ክፍት ቦታ ልታገኝ ትችላለህ።

ጉብኝት

ዎርዊክ

1 Kings Dr.

TUXEDO PARK, NY 10987

UNITED STATES

+1 845-524-3000

የጉብኝቱ ዋና ዋና ገጽታዎች

ያለአስጎብኚ የሚታይ ኤግዚቢሽን

  1. መጽሐፍ ቅዱስ እና መለኮታዊው ስም። ይህ ኤግዚቢሽን በቀላሉ የማይገኙ መጽሐፍ ቅዱሶችን እንዲሁም የአምላክን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ሙከራው የከሸፈው እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ መረጃዎችን የሚያስቃኝ ነው። በተጨማሪም ኤግዚቢሽኑ ሌሎች የጥንት መጽሐፍ ቅዱሶችንና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተያያዙ ቁሳቁሶችን የሚያሳይ ተሽከርካሪ ሙዚየም ይዟል።

  2. ለይሖዋ ስም የሚሆን ሕዝብ። ይህ ኤግዚቢሽን የይሖዋ ምሥክሮችን መንፈሳዊ ቅርስ የሚያሳይ ነው። በዚያ የሚገኙት ቁሳቁሶች፣ ሥዕሎች እና ባለታሪኮቹ የጻፏቸው ዘገባዎች ይሖዋ ሕዝቦቹ ፈቃዱን እንዲፈጽሙ ቀስ በቀስ የመራቸው፣ ያስተማራቸውና ያደራጃቸው እንዴት እንደሆነ ያሳያሉ።

  3. ዋናው መሥሪያ ቤት—በተግባር የተደገፈ እምነት። ይህ ኤግዚቢሽን የበላይ አካሉ ኮሚቴዎች የሚሠሩትን ነገሮች ያብራራል፤ በተጨማሪም የበላይ አካሉ ኮሚቴዎች የይሖዋ ምሥክሮች አንድ ላይ እንዲሰበሰቡ፣ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉ፣ መንፈሳዊ ምግብ እንዲመገቡና እርስ በርሳቸው እንዲዋደዱ የተሰጣቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ትእዛዝ እንዲፈጽሙ የረዱት እንዴት እንደሆነ ያሳያል።

በአስጎብኚ

ይህ ጉብኝት ቢሮዎችን እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃውን እንዲሁም የዎርዊክን ግቢ ያካትታል።

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ

ፓተርሰን

100 Watchtower Dr. (2891 Route 22)

PATTERSON, NY 12563

UNITED STATES

+1 845-306-1000

የጉብኝቱ ዋና ዋና ገጽታዎች

በጽሑፎቻችን ላይ የሚወጡ ሥዕሎች እንዲሁም የድምፅና ምሥል ቀረጻ የሚካሄድባቸውን ቦታዎች መጎብኘት። ጉብኝቱ ትምህርት ቤቶችን መጎብኘትንም ያካትታል።

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ

ዎልኪል

900 Red Mills Rd.

WALLKILL, NY 12589

UNITED STATES

+1 845-744-6000

የጉብኝቱ ዋና ዋና ገጽታዎች

በየዓመቱ ከ25 ሚሊዮን የሚበልጡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች ይታተማሉ። ከ360 በሚበልጡ ቋንቋዎች የተዘጋጁ ጽሑፎች በዓለም ዙሪያ ወደሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች እንዲሁም በዩናይትድ ስቴትስ፣ በካናዳና በካሪቢያን ለሚገኙ ከ15,000 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች ይላካሉ።

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ