በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የዎርዊክ ፎቶ ጋለሪ 2 (ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ 2014)

የዎርዊክ ፎቶ ጋለሪ 2 (ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ 2014)

አዲሱ የይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ 2014 ባለው ጊዜ ውስጥ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ በዚህ ፎቶ ጋለሪ አማካኝነት ተመልከት።

የዎርዊክ ግንባታ ሲጠናቀቅ ምን መልክ እንደሚኖረው የሚያሳይ ምስል። ከላይ ጀምሮ ከግራ ወደ ቀኝ፦

  1. የተሽከርካሪዎች ጥገና ሕንፃ

  2. የጎብኚዎች የመኪና ማቆሚያ

  3. የጥገና ሕንፃ እና የነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ

  4. መኖሪያ ሕንፃ ለ

  5. መኖሪያ ሕንፃ መ

  6. መኖሪያ ሕንፃ ሐ

  7. መኖሪያ ሕንፃ ሀ

  8. የቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃ

መስከረም 11, 2014—የጎብኚዎች የመኪና ማቆሚያ

ፋብሪካ ውስጥ የተዘጋጁ ለመኖሪያ ሕንፃ ሐ የሚሆኑ የብረት ጣሪያዎች።

መስከረም 18, 2014—የዎርዊክ የግንባታ ቦታ

ከግንባታ ቦታው በስተደቡብ በኩል ስተርሊንግ ፎረስት ሌክ (ብሉ ሌክ) ወደሚገኝበት ወደ ሰሜን አቅጣጫ የተነሳ ፎቶግራፍ። በአንድ ጊዜ 13 የሚያህሉ ዕቃ ማንሻ ክሬኖች በሥራ ላይ ተሰማርተው። ለመኖሪያ ሕንፃ ለ መሠረት የሚሆን አርማታ ሲሞላ።

መስከረም 26, 2014—የቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃ

ለመገጣጠም የተዘጋጁ የብረት ምሰሶዎችና ተሸካሚዎች። የቢሮዎችና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃው ክፍትና ሰፊ ቦታ ያለው መሆኑ ግንባታው እንዲፋጠን አስተዋጽኦ አድርጓል።

ጥቅምት 9, 2014—የዎርዊክ የግንባታ ቦታ

ሠራተኞቹ ለመኖሪያ ሕንፃ ሐ የተዘጋጀውን ውኃ እንዳያስገባ ተደርጎ የተሠራ የብረት ጣሪያ ሲገጣጥሙ። ከኋላና በስተ ግራ በኩል የሚገጠመው ጣሪያ ሲዘጋጅ።

ጥቅምት 15, 2014—የቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃ

የግንባታ ሠራተኞች በደቡብ ምዕራብ ጫፍ ላለው ሕንፃ የብረት ምሰሶዎች ሲያቆሙ። ኩሽናና የመመገቢያ አዳራሽ፣ የልብስ ንጽሕና ክፍልና ሌሎች ድጋፍ ሰጪ የሥራ ክፍሎች የሚኖሩት በዚህ የሕንፃው ክፍል ነው።

ጥቅምት 15, 2014—የዎርዊክ የግንባታ ቦታ

የፍሳሽ ማስወገጃውን እየሠራ ያለ አንድ ወንድም ብሩሽ ሲቀበል።

ጥቅምት 20, 2014—የዎርዊክ የግንባታ ቦታ

ይህ የናሙና ግድግዳ ሸክላዎቹ የሚገጣጠሙበትንና የሚደረደሩበትን መንገድ እንዲሁም የሸክላውን ቀለም ለመወሰን ያገለግላል። አዲስ የሚመጡ ግንበኞች የሚሠሩበትን መንገድ ለማሳየትም ያገለግላል። ይህ ግድግዳ የታለመለትን ዓላማ ካሳካ በኋላ ይፈርሳል።

ጥቅምት 31, 2014—መኖሪያ ሕንፃ ሐ

የሕንፃውን ግማሽ የሚሸፍነው አስቀድሞ የተዘጋጀ ጣሪያ ወደሚፈለግበት ቦታ በዕቃ ማንሻ ክሬን ይወሰዳል። በዚህ መልክ በእያንዳንዱ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ የተገጠሙት ጣሪያዎች ከሩቅ ሲታዩ ጠፍጣፋ ቅርጽ አላቸው።

ኅዳር 7, 2014—የጥገና ሕንፃ እና የነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ

ወደ 95,000 ሊትር (25,000 ጋሎን) የሚደርስ ነዳጅ የመያዝ አቅም ያለው ጋን የሚቀመጥበት ቦታ ላይ እንዲያርፍ ሲደረግ። ማሞቂያዎቹ የሚያስፈልጋቸውን ነዳጅ የሚያገኙት ከእነዚህ ጋኖች ነው።

ኅዳር 12, 2014—መኖሪያ ሕንፃ ሐ

ሕንፃውን ከደቡብ አቅጣጫ ሆነን ስንመለከተው፤ ብሉ ሌክ ከፎቶው ቀኝ ጠርዝ ላይ ይታያል። የሕንፃዎቹ ውጨኛ ክፍል አምሮ እንዲታይ ለማድረግ የተለያዩ ቀለሞችና አንዳንድ ማሳመሪያዎች ጥቅም ላይ ውለዋል።

ኅዳር 21, 2014—የጥገና ሕንፃ እና የነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ

በቧንቧ ሥራ ክፍል ውስጥ የሚሠሩ አንድ ባልና ሚስት የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ሲዘረጉ።

ኅዳር 28, 2014—የቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃ

ጣሪያ ላይ ያለውን በረዶ ሲያጸዱ።

ታኅሣሥ 1, 2014—የጥገና ሕንፃ እና የነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ

አንድ ባልና ሚስት የቧንቧ መስመር ፕላኑን እየተመለከቱ።

ታኅሣሥ 10, 2014—የጥገና ሕንፃ እና የነዋሪዎች የመኪና ማቆሚያ

በረዶ በሚጥልበት ቀን የቁፋሮ፣ መስመሮችን የመዘርጋት እና አርማታ የመሙላት ሥራ ሲከናወን። ከላይ በግራ በኩል የቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃ አንዳንድ ክፍሎች በፕላስቲክ ተሸፍነው ይታያሉ፤ ይህም የተስተካከለ ሙቀት እንዲኖር የሚጠይቁ ሥራዎችን ለምሳሌ አርማታ የመሙላትና ሕንፃው በእሳት እንዳይጎዳ የሚከላከሉ ነገሮችን በክረምት ወራት ጭምር ለመሥራት ያስችላል።

ታኅሣሥ 12, 2014—መኖሪያ ሕንፃ መ

ሠራተኞች ከውጪ ያለው ግድግዳ ተሠርቶ ከመጠናቀቁ በፊት በአርማታ የተሞላውን ምሰሶ በፕላስቲክ ሲሸፍኑ።

ታኅሣሥ 15, 2014—የዎርዊክ የግንባታ ቦታ

ሕንፃው በስተ በምዕራብ በኩል ሲታይ። የመኖሪያ ሕንፃዎቹ ፎቶው ላይ በላይ በኩል ይታያሉ። ፎቶው መሃል ላይ የሚታየው ትልቁ ነጭ ፎቅ የቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃ ነው። በሕንፃው አካባቢ ያለው ደን በግንባታው ምክንያት ምንም ጉዳት አልደረሰበትም፤ የድርጅቱ አጠቃላይ ይዞታ ወደ 100 ሄክታር ገደማ ሲሆን ለሕንፃዎቹ ግንባታ የዋለው ቦታ 20 በመቶ እንኳ አያክልም።

ታኅሣሥ 15, 2014—የዎርዊክ የግንባታ ቦታ

በስተ ምሥራቅ በኩል ያለው እይታ፤ የመኖሪያ ሕንፃ ሐ እና መ ፎቶው ላይ ከታች በኩል ይታያሉ። የሕንፃ ተቋራጮች በመኖሪያ ሕንፃ ሐ ላይ የሚከናወነውን ጣሪያ የማልበስ ሥራ አጠናቀዋል።

ታኅሣሥ 25, 2014—መኖሪያ ሕንፃ ሐ

አንድ የእንጨት ሥራ ባለሞያ የናሙና ክፍል ውስጥ የወለል ንጣፍ እያነጠፈ። የእያንዳንዱ መኖሪያ ክፍል የማጠናቀቂያ ሥራ አስቀድሞ በተዘጋጀለት ቅንብር መሠረት ይካሄዳል። ይህም ቀለም መቀባትን፣ ምንጣፍ ማንጠፍን፣ የወለል ሸክላና ንጣፍ ሥራን እንዲሁም የወጥ ቤት መደርደሪያዎችን መግጠምን ይጨምራል።

ታኅሣሥ 31, 2014—የቢሮዎች እና የአገልግሎት መስጫ ሕንፃ

ፍሳሽን በተገቢው መንገድ ለማስወገድ እንዲቻል የወለሉ አርማታ ከተሞላ በኋላ ወለሉ የተስተካከለው በእጅ ነው።

ታኅሣሥ 31, 2014—መኖሪያ ሕንፃ ሐ

የ77 ዓመት ቴክኒሽያን የፋይበር ኦፕቲክ መስመር ሲዘረጋ። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የተዘረጋው መስመር በአጠቃላይ 32 ኪሎ ሜትር ይሆናል።