በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮዎች ተዋሃዱ

የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮዎች ተዋሃዱ

ከመስከረም 2012 ወዲህ ከ20 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮዎች በሌሎች ትላልቅ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ሥር እንዲጠቃለሉ ተደረገ።

በተጨማሪም በሰርቢያና በመቄዶንያ አዳዲስ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ተቋቁመዋል። እንዲህ ያሉ ለውጦች የተደረጉት በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች የተነሳ ነው።

1. ቴክኖሎጂ ሥራው እንዲቀል አድርጓል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በመገናኛና በኅትመት ቴክኖሎጂ ረገድ የታየው እመርታ በትላልቅ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል እንዲቀንስ አድርጓል። በትላልቅ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች ብዛት ሲቀንስ ተጨማሪ የመኖሪያ ክፍሎችን ማግኘት ተቻለ፤ ይህም አነስተኛ በሆኑ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ የሚሠሩ ሰዎችን ለማኖር የሚያስችል ነው።

የቅርንጫፍ ቢሮዎቹ መዋሃድ ተሞክሮ ያላቸው በርካታ የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስን ለማስተማሩ ሥራ ድጋፍ እንዲሰጡ አድርጓል። ለምሳሌ ያህል በሆንዱራስ፣ በኒካራጓ፣ በኤል ሳልቫዶር፣ በኮስታ ሪካ፣ በጓቲማላ እና በፓናማ የሚከናወነውን የስብከት ሥራ የሚከታተለው በሜክሲኮ የሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ሆኗል። በዚህም የተነሳ በእነዚህ ስድስት አገሮች ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ተዘግተዋል።

በእነዚህ ስድስት ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ ይሠሩ የነበሩ 40 የይሖዋ ምሥክሮች በሜክሲኮ ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል። ሌሎች 95 የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች ደግሞ በትውልድ አገራቸው የሙሉ ጊዜ ሰባኪዎች ሆነዋል።

በማዕከላዊ አሜሪካ በሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች በሜክሲኮ ቅርንጫፍ ቢሮ ሥር በተለያዩ የትርጉም ቢሮዎች ውስጥ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በፓናማ የሚኖሩ 20 ገደማ የሚሆኑ ተርጓሚዎች የይሖዋ ምሥክሮችን ጽሑፎች በተለያዩ የአገሬው ቋንቋዎች እየተረጎሙ ነው። በጓቲማላ በሚገኘው የቀድሞ ቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ደግሞ 16 የይሖዋ ምሥክሮች ጽሑፎችን በአራት የአገሩ ቋንቋዎች ይተረጉማሉ። በማዕከላዊ አሜሪካ በሚገኙ አገሮች የተደረገው ይህ ለውጥ በቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ የሚሠሩ ሰዎች ብዛት ከ300 ወደ 75 ገደማ እንዲቀንስ አድርጓል።

2. በስብከቱ ሥራ ላይ ብዙ ጊዜ የሚያሳልፉ ተጨማሪ ሰባኪዎችን ማግኘት ይቻላል።

ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ እንዲሸጋሸጉ መደረጋቸው በትናንሽ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ ያገለግሉ የነበሩ ብቃት ያላቸው ወንጌላውያን ምሥራቹን በመስበኩ ሥራ ላይ እንዲያተኩሩ አስችሏል።

በስብከቱ ሥራ ላይ የበለጠ ጊዜ እንዲያሳልፍ የተመደበ በአፍሪካ የሚገኝ አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ላይ ከአዲሱ ሕይወቴ ጋር መላመድ ከባድ ሆኖብኝ ነበር። ሆኖም በየቀኑ በስብከቱ ሥራ መካፈሌ ከጠበቅሁት በላይ ደስታ እና በረከት አስገኝቶልኛል። በአሁኑ ጊዜ 20 ሰዎችን መጽሐፍ ቅዱስ እያስተማርኩ ነው፤ ከእነሱ መካከል አንዳንዶቹ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀምረዋል።