በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የፎቶ ጋለሪልጆች ቪዲዮዎቹን ወደዋቸዋል

የፎቶ ጋለሪልጆች ቪዲዮዎቹን ወደዋቸዋል

የይሖዋ ወዳጅ ሁን የሚል ርዕስ ያለው ተከታታይ ቪዲዮ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል፤ ይህ ቪዲዮ መዝሙሮችን እንዲሁም ካሌብና ሶፊያ የተባሉ ሁለት የአኒሜሽን ገጸ ባሕርያትን የሚያሳይ ነው። ወላጆችም ሆኑ ልጆች፣ ለቪዲዮዎቹ ያላቸውን አድናቆት የሚገልጽ መልእክት ጽፈዋል። ልጆች ከላኳቸው አስተያየቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

  • “‘አዳምጥ፣ ታዘዝ፤ ትባረካለህ’ ለሚለው ዲቪዲ አመሰግናለሁ። ከአሻንጉሊቴ ጋር ሆኜ በየቀኑ አየዋለሁ።”—ዛክ፣ የ5 ዓመት ልጅ

  • “አዲሱ መዝሙር ይሖዋ እንደሚወደኝና በማንኛውም ጊዜ ወደ እሱ እንድጸልይ የሚፈልግ መሆኑን እንዳውቅ አድርጎኛል።”—ሚካሪያ፣ የ6 ዓመት ልጅ

  • “ወላጆቼን መታዘዝና ዕቃዎቼን በሥርዓት ማስቀመጥ እንዳለብኝ ተምሬያለሁ። ይህን የልጆች ፊልም ስላዘጋጃችሁልን አመሰግናለሁ።”—ኒኮል፣ የ8 ዓመት ልጅ

  • “ላዘጋጃችሁት ቪዲዮ በጣም አመሰግናለሁ። በጣም የሚያስቅና የሚያዝናና ነው፤ ደስ ይላል።”—መኬንዚ፣ የ5 ዓመት ልጅ

  • “የይሖዋ ወዳጅ ሁን የሚሉትን ቪዲዮዎች እወዳቸዋለሁ። በየቀኑ አያቸዋለሁ። ይሄ ሐሳብ እንዲመጣላችሁ ስላደረገ ይሖዋ ጥሩ አምላክ ነው።”—አቫ፣ የ8 ዓመት ልጅ

  • “ቪዲዮዎቹን ማየት በጣም ደስ ይለኛል። መዝሙሮቹን በሙሉ ለመማር እየሞከርኩ ነው። እነዚህ ቪዲዮዎች ይሖዋን እንድወደው ያደርጉኛል።”—ዴቨን፣ የ4 ዓመት ልጅ

  • “ቀጣዩ የካሌብ ቪዲዮ እስኪወጣ በጣም ጓጉቻለሁ! በዚሁ ቀጥሉ!”—ቫንስ፣ የ8 ዓመት ልጅ

አውስትራሊያ—ሺሎ፣ የ6 ዓመት ልጅ

ትምህርት 12፦ ካሌብና ሶፊያ ቤቴልን ጎበኙ

አውስትራሊያ—ሲዬና፣ የ8 ዓመት ልጅ

መዝሙር 106፦ የይሖዋ ወዳጅ መሆን

ብራዚል—ኤድዋርዶ፣ የ10 ዓመት ልጅ

ትምህርት 13፦ ይሖዋ ደፋር እንድትሆን ይረዳሃል

ጀርመን—ምሼል፣ የ11 ዓመት ልጅ

ትምህርት 10፦ ደግ ሁን፤ ያለህን አካፍል

ጀርመን—ፕሪስላ፣ የ8 ዓመት ልጅ

ትምህርት 11፦ በነፃ ይቅር በል

ጃፓን—ሚኩ፣ የ7 ዓመት ልጅ

ትምህርት 13፦ ይሖዋ ደፋር እንድትሆን ይረዳሃል

ጃፓን—ቶሞአኪ፣ የ10 ዓመት ልጅ

ትምህርት 6፦ እባክህ እና አመሰግናለሁ

ሜክሲኮ—ሳሙኤል፣ የ7 ዓመት ልጅ

ትምህርት 9፦ ‘ሁሉንም ነገሮች የፈጠረው ይሖዋ ነው’

ዩናይትድ ስቴትስ—አድሪያና፣ የ6 ዓመት ልጅ

መዝሙር 92፦ “ቃሉን ስበክ”

ዩናይትድ ስቴትስ—አንቶኒ፣ የ11 ዓመት ልጅ

ትምህርት 2፦ ይሖዋን ታዘዝ