በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቂት ገጾች፣ ብዙ ቋንቋዎች

ጥቂት ገጾች፣ ብዙ ቋንቋዎች

ከጥር 2013 አንስቶ በየወሩ የሚወጡት ንቁ! እና ለሕዝብ የሚሰራጨው መጠበቂያ ግንብ መጽሔቶች ገጽ ከ32 ወደ 16 እንዲቀንስ ይደረጋል።

በመጽሔቶቹ ላይ የሚወጡ ርዕሶች በመቀነሳቸው መጽሔቶቹ የሚተረጎሙባቸው ቋንቋዎች ብዛት እንደሚጨምር ይጠበቃል። ለምሳሌ ያህል፣ የታኅሣሥ 2012 ንቁ! በ84 ቋንቋዎች የታኅሣሥ 2012 መጠበቂያ ግንብ ደግሞ በ195 ቋንቋዎች ታትሞ ነበር። ይሁንና በጥር 2013 ንቁ! በ98 ቋንቋዎች መጠበቂያ ግንብ ደግሞ በ204 ቋንቋዎች ታትሟል።

የሚጠናው የመጠበቂያ ግንብ እትም ግን ባለ 32 ገጽ እንደሆነ ይቀጥላል።

የሚታተሙት ገጾች ቀነሱ፤ ድረ ገጹ ላይ የሚወጡ ርዕሶች ጨመሩ

ታትመው በሚወጡት መጽሔቶቻችን ላይ የተደረገው ለውጥ www.jw.org የተባለውን ድረ ገጻችንን በሁለት መንገዶች ይነካዋል።

  1. ቀደም ሲል በመጽሔቶቻችን ላይ ይወጡ የነበሩ አንዳንድ ዓምዶች አሁን በድረ ገጹ ላይ ብቻ ይወጣሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ለሕዝብ በሚሰራጨው መጠበቂያ ግንብ እትም ላይ ይወጡ የነበሩት “ለታዳጊ ወጣቶች” እና “መጽሐፍ ቅዱስን መማሪያዬ” የተባሉት ዓምዶች ብሎም የጊልያድ ትምህርት ቤት ምረቃ ሪፖርት እንዲሁም በንቁ! መጽሔት ላይ ይወጡ የነበሩት “ቤተሰብ የሚወያይበት” እና “የወጣቶች ጥያቄ” የተባሉት ዓምዶች አሁን የሚወጡት በድረ ገጹ ላይ ብቻ ይሆናል።

  2. የመጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች በተጨማሪ የኤሌክትሮኒክ ፎርማት ተዘጋጅተው መውጣት ይጀምራሉ። ላለፉት ዓመታት በ​PDF የተዘጋጁ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶች www.jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ ሲወጡ ቆይተዋል። አሁን እነዚህ መጽሔቶች በ​HTML ፎርማት መዘጋጀት ይጀምራሉ፤ ይህም መጽሔቶቹን በኮምፒውተርም ሆነ በተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ መክፈትና ማንበብ ቀላል እንዲሆን ያደርጋል። በተጨማሪም ኢንተርኔት ላይ ከ430 በሚበልጡ ቋንቋዎች የወጡ ሌሎች ጽሑፎቻችንን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል።