በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አንዳንድ ፊልሞችን፣ መጻሕፍትን ወይም ዘፈኖችን ትከለክላላችሁ?

አንዳንድ ፊልሞችን፣ መጻሕፍትን ወይም ዘፈኖችን ትከለክላላችሁ?

በፍጹም። ድርጅታችን ፊልሞችን፣ መጻሕፍትን ወይም ሙዚቃዎችን አንድ በአንድ በመመርመር አባላቱ ሊዝናኑባቸው የሚችሉ ነገሮችን የሚገልጽ ዝርዝር መመሪያ አያወጣም። ለምን?

● መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ሰው ‘የማስተዋል ችሎታውን’ በማሠልጠን ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር እንዲለይ ያበረታታል።ዕብራውያን 5:14

● ቅዱሳን መጻሕፍት አንድ ክርስቲያን ከመዝናኛ ምርጫው ጋር በተያያዘ ሊያስብባቸው የሚገቡ አንዳንድ መመሪያዎችን ይዘዋል። * በሁሉም የሕይወታችን ዘርፍ ዋናው ግባችን ‘በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ምን እንደሆነ ምንጊዜም መርምሮ ማረጋገጥ’ ነው።ኤፌሶን 5:10

● መጽሐፍ ቅዱስ የቤተሰብ ራሶች የተወሰነ ሥልጣን እንዳላቸው ስለሚያስተምር አንድ የቤተሰብ ራስ የቤተሰቡ አባላት ሊዝናኑባቸው የማይገቡ ነገሮችን የመምረጥ ኃላፊነት አለበት። (1 ቆሮንቶስ 11:3፤ ኤፌሶን 6:1-4) ከቤተሰብ ውጪ ግን ማንም ሰው አንድን ፊልም፣ ዘፈን ወይም አርቲስት በማውገዝ አንድ መዝናኛ ተገቢ መሆን አለመሆኑን የመወሰን መብት የለውም።ገላትያ 6:5

^ አን.4 ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከመናፍስታዊ ድርጊት፣ ከፆታ ብልግናና ከዓመፅ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ያወግዛል።ዘዳግም 18:10-13፤ ኤፌሶን 5:3፤ ቆላስይስ 3:8