በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የምትድኑት እናንተ ብቻ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል?

የምትድኑት እናንተ ብቻ እንደሆናችሁ ይሰማችኋል?

በፍጹም። ባለፉት ዘመናት በዚህች ምድር ላይ የኖሩና የይሖዋ ምሥክር ያልነበሩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መዳን የሚያገኙበት አጋጣሚ ይከፈትላቸዋል። አምላክ ቃል በገባልን አዲስ ዓለም ውስጥ “ጻድቃንም ሆኑ ዓመፀኞች ከሞት እንደሚነሱ” መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (የሐዋርያት ሥራ 24:15) በተጨማሪም በዛሬው ጊዜ በሕይወት ያሉ ብዙ ሰዎች ወደፊት አምላክን ማገልገል ሊጀምሩ ስለሚችሉ እነሱም ቢሆኑ መዳን ያገኛሉ። ዞሮ ዞሮ ማን ይድናል ወይም ማን አይድንም የሚለውን ፍርድ መስጠት የእኛ ቦታ አይደለም። ይህን የማድረግ መብት ያለው ኢየሱስ ነው።ዮሐንስ 5:22, 27