በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

በሚስዮናዊነት አገልግሎት ትካፈላላችሁ?

በሚስዮናዊነት አገልግሎት ትካፈላላችሁ?

አዎ። ሁሉም የይሖዋ ምሥክሮች የሚኖሩት የትም ይሁን የት ለሚያገኟቸው ሰዎች ስለ እምነታቸው የመናገር ልማድ ስላላቸው የሚስዮናዊነት መንፈስ እንዳላቸው ያሳያሉ።​—⁠ማቴዎስ 28:19, 20

በተጨማሪም አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች በአገራቸው ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ያልሰሙ በርካታ ሰዎች ወደሚኖሩበት አካባቢ በራሳቸው ወጪ እየተመላለሱ ወይም እዚያው እየኖሩ ይሰብካሉ። ሌሎች ደግሞ አገልግሎታቸውን ለማስፋት ሲሉ ወደ ሌላ አገር ይሄዳሉ። ሁሉም፣ ኢየሱስ “እስከ ምድር ዳር ድረስ ምሥክሮቼ ትሆናላችሁ” በማለት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማድረግ በመቻላቸው ደስተኞች ናቸው።​—⁠የሐዋርያት ሥራ 1:8

በ1943 ለአንዳንድ ሚስዮናውያን ልዩ ሥልጠና ለመስጠት የሚያስችል ትምህርት ቤት አቋቁመናል። ከዚያ ጊዜ አንስቶ ከ8,000 በላይ የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች ጊልያድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ተብሎ በሚጠራው በዚህ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብተው ሠልጥነዋል።