በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ሃይማኖታችሁ ከአሜሪካ የመጣ ኑፋቄ ነው?

ሃይማኖታችሁ ከአሜሪካ የመጣ ኑፋቄ ነው?

ዋናው መሥሪያ ቤታችን የሚገኘው በአሜሪካ ነው። ሃይማኖታችን ግን ከአሜሪካ የመጣ ኑፋቄ አይደለም፤ እንዲህ የምንለው በሚከተሉት ምክንያቶች የተነሳ ነው፦

  • አንዳንዶች ኑፋቄ የሚለውን ቃል ቀደም ሲል ከነበረ ሃይማኖት ተገንጥሎ የወጣን ቡድን ለማመልከት ይጠቀሙበታል። የይሖዋ ምሥክሮች እምነት ከሌላ ሃይማኖት ተገንጥሎ የወጣ አይደለም። ከዚህ ይልቅ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረውን የክርስትና እምነት መልሰን እንዳቋቋምን ይሰማናል።
  • የይሖዋ ምሥክሮች ከ230 በሚበልጡ አገሮች አገልግሎታቸውን በቅንዓት ያከናውናሉ። የምንኖረው የትም ይሁን የት በዋነኝነት ታማኝነታችንን የምናሳየው ለይሖዋ አምላክና ለኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ ለአሜሪካ መንግሥት ወይም ለሌላ ለማንኛውም ሰብዓዊ ገዥ አይደለም።ዮሐንስ 15:19፤ 17:15, 16
  • ትምህርቶቻችን የተመሠረቱት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንጂ በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የሃይማኖት መሪዎች በጻፉት መመሪያ ላይ አይደለም።1 ተሰሎንቄ 2:13
  • የምንከተለው ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፤ የምንከተለው ምንም ዓይነት ሰብዓዊ መሪ የለም።ማቴዎስ 23:8-10