በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ሴት ሰባኪዎች አሏችሁ?

ሴት ሰባኪዎች አሏችሁ?

አዎ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶችን ጨምሮ ሁሉም የይሖዋ ምሥክሮች ሰባኪ ወይም አገልጋይ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ‘ብዙ ሴቶች ዜናውን እያሰራጩ’ ነው።መዝሙር 68:11 የ1980 ትርጉም

የይሖዋ ምሥክር የሆኑ ሴቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሴቶች የተዉትን ምሳሌ ይከተላሉ። (ምሳሌ 31:10-31) አነዚህ ሴቶች በጉባኤ ውስጥ የመሪነት ቦታ ለመያዝ ባይሞክሩም በስብከቱ ሥራ ሙሉ ተሳትፎ ያደርጋሉ። ከዚህም ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ለልጆቻቸው ያስተምራሉ። (ምሳሌ 1:8) በተጨማሪም በቃልም ሆነ በተግባር ሰዎች ላይ በጎ ተጽዕኖ ለማሳደር ተግተው ይሠራሉ።ቲቶ 2:3-5