በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ቀደም ሲል የእናንተ ሃይማኖት አባል የነበረን ሰው ታገላላችሁ?

ቀደም ሲል የእናንተ ሃይማኖት አባል የነበረን ሰው ታገላላችሁ?

ተጠምቀው የይሖዋ ምሥክር ከሆኑ በኋላ ለሌሎች መስበካቸውን አልፎ ተርፎም ከእምነት ባልንጀሮቻቸው ጋር መሰብሰባቸውን ያቆሙ ክርስቲያኖችን አናገላቸውም። እንዲያውም እነሱን ፈልገን ለማግኘትና መንፈሳዊ ቅንዓታቸውን መልሰው እንዲያቀጣጥሉ ለመርዳት ጥረት እናደርጋለን።

ከባድ ኃጢአት የፈጸመን ሰው ወዲያውኑ አናስወግድም። ይሁንና አንድ የተጠመቀ የይሖዋ ምሥክር የመጽሐፍ ቅዱስን የሥነ ምግባር ደንቦች መጣስ ልማድ ካደረገና ንስሐ የማይገባ ከሆነ ሊገለል ወይም ሊወገድ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወጡት” በማለት ግልጽ መመሪያ ይሰጣል።1 ቆሮንቶስ 5:13

አንድ ሰው ቢወገድና ሚስቱና ልጆቹ ግን የይሖዋ ምሥክር ቢሆኑስ? መንፈሳዊ ግንኙነታቸው ቢቋረጥም የሥጋ ዝምድናቸው ይቀጥላል። የትዳር ሕይወታቸውና መደበኛ የሆነው የቤተሰብ ሕይወታቸው እንዳለ ይቀጥላል።

የተወገዱ ግለሰቦች በመንፈሳዊ ስብሰባዎቻችን ላይ መገኘት ይችላሉ። እንዲሁም ከፈለጉ የጉባኤ ሽማግሌዎች መንፈሳዊ ምክር ሊሰጧቸው ይችላሉ። ምክር የሚሰጥበት ዓላማ ግለሰቡ በድጋሚ የይሖዋ ምሥክር ለመሆን የሚያስፈልገውን ብቃት እንዲያሟላ ለመርዳት ነው። የተወገዱ ሰዎች ከመጥፎ ሥነ ምግባር እስከራቁና በመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ መሠረት ለመኖር ልባዊ ፍላጎት እንዳላቸው በተግባር እስካሳዩ ድረስ ተመልሰው የጉባኤው አባል ለመሆን የሚያቀርቡትን ጥያቄ ምንጊዜም በደስታ እንቀበላለን።