በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የድርጅታችሁ መሥራች ማን ነው?

የድርጅታችሁ መሥራች ማን ነው?

የይሖዋ ምሥክሮች ድርጅት በዘመናችን እቅስቃሴ የጀመረው በ19ኛው መቶ ዘመን መገባደጃ ላይ ነው። በወቅቱ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት በሆነው በፔንስልቬንያ ውስጥ በምትገኘው በፒትስበርግ ከተማ አቅራቢ የሚኖሩ ቁጥራቸው ጥቂት የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች መጽሐፍ ቅዱስን ጥልቀት ባለው መንገድ መመርመር ጀመሩ። አብያተ ክርስቲያናት የሚያስተምሩትን ነገር ከትክክለኛው የመጽሐፍ ትምህርት ጋር በማነጻጸር ልዩነቱን ለማወቅ ጥረት ያደርጉ ነበር። ከዚያም የተረዱትን ነገር በመጻሕፍት፣ በጋዜጦችና በአሁኑ ጊዜ የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ በመባል በሚጠራው መጽሔት ላይ እያሳተሙ ማውጣት ጀመሩ።

ከእነዚህ ቅን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች መካከል ቻርልስ ቴዝ ራስል ይገኝበታል። በወቅቱ ራስል መጽሐፍ ቅዱስ የማስተማሩን ሥራ ይመራ እንዲሁም የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የመጀመሪያው አዘጋጅ በመሆን ያገለግል የነበረ ቢሆንም አዲስ ሃይማኖት አልመሠረተም። የራስልና የሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች (በወቅቱ የይሖዋ ምሥክሮች ይጠሩበት የነበረ ስም ነው) ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን ትምህርቶች ማስፋፋትና በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበረው የክርስቲያን ጉባኤ የተወውን አርዓያ መከተል ነው። የክርስትና መሥራች ኢየሱስ በመሆኑ የድርጅታችንም መሥራች እሱ እንደሆነ እናምናለን።ቆላስይስ 1:18-20