በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለሥራችሁ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የምታገኙት እንዴት ነው?

ለሥራችሁ የሚያስፈልገውን ገንዘብ የምታገኙት እንዴት ነው?

ለስብከቱ ሥራ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በዋነኝነት የምናገኘው የይሖዋ ምሥክሮች በፈቃደኝነት ከሚያደርጉት መዋጮ ነው። በስብሰባዎቻችን ላይ ሙዳየ ምጽዋት አይዞርም፤ እንዲሁም አባላቱ አሥራት አይጠየቁም። (ማቴዎስ 10:7, 8) ከዚህ ይልቅ በመሰብሰቢያ ቦታዎቻችን የመዋጮ ሣጥኖች ይዘጋጃሉ፤ ይህም አንድ ሰው መዋጮ ማድረግ በሚፈልግበት ጊዜ ያሰበውን ገንዘብ ለመጨመር ያስችለዋል። መዋጮ ያደረጉ ሰዎች ስማቸው አይለፈፍም።

ወጪዎቻችንን መሸፈን የቻልንበት አንዱ ምክንያት በክፍያ የሚሠሩ የሃይማኖት መሪዎች ስለሌሉን ነው። በተጨማሪም የይሖዋ ምሥክሮች ከቤት ወደ ቤት እየሄዱ የሚሰብኩት ተከፍሏቸው አይደለም። የአምልኮ ቦታዎቻችንም ቢሆኑ ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁ አይደሉም፤ ከዚህ ይልቅ ቀለል ያሉ ሆኖም ማራኪ ናቸው።

ወደ ቅርንጫፍ ቢሮዎች የሚላኩትን መዋጮዎች በሙሉ የምንጠቀምባቸው በተፈጥሮ አደጋዎች የተጠቁትን ለመርዳት፣ ሚስዮናውያንንና ተጓዥ አገልጋዮችን ለመደገፍ፣ በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮች ውስጥ የአምልኮ ቤቶችን ለመገንባት እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስንና ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎችን ለማተምና ለመላክ ነው።

ማንኛውም ሰው እንደምርጫው ማለትም የጉባኤውን ወጪ ለመሸፈን አሊያም ለዓለም አቀፉ ሥራ እንዲውል መዋጮ ማድረግ ይችላል፤ ወይም ደግሞ ለሁለቱም ዓላማ እንዲውል መዋጮ ማድረግ ይችላል። እያንዳንዱ ጉባኤ በየጊዜው የሒሳብ ሪፖርት ለአባላቱ ያቀርባል።