በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሰዎች የአምላክ ቃል ሕይወታቸውን እንዴት እንደለወጠው የተናገሩባቸውን እነዚህን ተሞክሮዎች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ትርጉም ያለው ሕይወት

በሕይወቴ ደስተኛ ሆንኩ

ከልጅነቱ ጀምሮ የበታችነት ስሜት ያጠቀው የነበረን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ የረዳው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

በአምላክ እርዳታ ትዳራችንን መልሰን ገነባን

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች፣ በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ፍቱን መድኃኒት ናቸው።

እውነተኛ ሀብት አገኘሁ

አንድ ስኬታማ የንግድ ኃላፊ ከሀብትና ከገንዘብ የበለጠ ዋጋ ያለው ነገር ያገኘው እንዴት ነው?

ሁዋን ፓብሎ ስርሜንዮ፦ ይሖዋ ትርጉም ያለው ሕይወት እንድመራ ረድቶኛል

በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን አሳዛኝ ክስተቶች ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ጠባሳ ትተውብን ሊያልፉ ይችላሉ። ሁዋን ፓብሎ የልጅነት ሕይወቱ አስቸጋሪ የነበረ ቢሆንም ደስተኛና ትርጉም ያለው ሕይወት መምራት የቻለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ጆኒ እና ጊዲየን፦ ከጠላትነት ወደ ወንድማማችነት

በአንዳንድ አካባቢዎች የዘር ጥላቻ እጅግ ተስፋፍቷል። በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ጭፍን ጥላቻን ማሸነፍ የቻሉት እንዴት ነው?

በስብሰባ አዳራሽ የተደረገልንን አቀባበል መቼም ቢሆን አንረሳውም

ስቲቭ ለመጀመሪያ ጊዜ በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ በተገኘበት ወቅት የተደረገለትን አቀባበል አሁንም ድረስ በደንብ ያስታውሰዋል።

ፍቅር ጥላቻን ድል ማድረግ ይችላል?

ጭፍን ጥላቻን ማስወገድ ከባድ ሊሆን ይችላል። አንድ አይሁዳዊና አንድ ፍልስጤማዊ ይህን ማድረግ የቻሉት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ግልጽና አሳማኝ መልስ አስደነቀኝ

ኧርነስት ሎዲ ከሕይወት ጋር በተያያዘ ለነበሩት አንዳንድ ጥያቄዎች መልስ አግኝቷል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያገኘው ግልጽ መልስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ እውነተኛ ተስፋ እንዲኖረው ረድቶታል።

መከራ ሲደርስባችሁ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጡ!

ዶሪስ፣ አምላክ በሰዎች ላይ መከራ እንዲደርስ የፈቀደው ለምን እንደሆነ ማወቅ ትፈልግ ነበር። መልሱን ከየት እንዳገኘች ማወቅ ትፈልጋለህ?

ሦስት ጥያቄዎች ሕይወቴን ለወጡት

ዶሪስ ኤልድረድ ለጥያቄዎቿ አርኪ መልስ ያገኘችው ከተማሪዋ ነው፤ ታሪኳን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ሞትን እፈራ ነበር!

ኢቮን ክዎሪ ‘የተፈጠርኩት ለምንድን ነው?’ የሚለው ጥያቄ ያሳስባት ነበር። የዚህን ጥያቄ መልስ ማወቋ ሕይወቷን ለውጦታል።

ይሖዋ ብዙ ነገር አድርጎልኛል

በልጅነቷ የፆታ ጥቃት ሰለባ የነበረችው ክሪስታል ከአምላክ ጋር ወዳጅነት እንድትመሠርት እንዲሁም ትርጉም ያለው ሕይወት እንድትመራ የረዳት የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት መማሯ ነው?

አሁን በራሴ አላፍርም

ኢዝሬል ማርቲኔዝ ሥር የሰደደ የበታችነት ስሜትን ማሸነፍና ለራሱ አክብሮት ማዳበር የቻለው እንዴት ነው?

ይሖዋ መስማት ለተሳናቸው እንደሚያስብ ተምሬያለሁ

ጄሰን መስማት የተሳነው ቢሆንም ይህ እክል ከአምላክ ጋር ዝምድና እንዳይመሠርት እንቅፋት አልሆነበትም።

በመጨረሻ ከአባቴ ጋር ሰላም ፈጠርን

ረኔ ዕፅ መውሰድና አልኮል ከመጠን በላይ መጠጣት የጀመረው ለምን እንደሆነና እነዚህን ልማዶቹን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ የቻለው እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

አሁን ሌሎችን መርዳት እንደምችል ይሰማኛል

ሁልዮ ኮርዮ ከደረሰበት አሳዛኝ አደጋ የተነሳ አምላክ ስለ እሱ ግድ እንደማይሰጠው ይሰማው ነበር። ሆኖም በዘጸአት 3፡7 ላይ የሚገኘው ጥቅስ አመለካከቱን እንዲቀይር ረድቶታል።

ሕይወቴ በራሴ ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር

ክሪስቶፍ ባወር በአንዲት ትንሽ ጀልባ ተጠቅሞ የአትላንቲክ ውቅያኖስን ሲያቋርጥ አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈው መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ነበር። ካነበበው ነገር ምን ትምህርት አገኝ?

የፍትሕ መዛባትን መታገል እፈልግ ነበር

ራፊካ የፍትሕ መዛባትን ለመታገል የተቋቋመን አንድ ቡድን ተቀላቅላ ነበር። ሆኖም ሰላምና ፍትሕ ማምጣት የሚችለው የአምላክ መንግሥት ብቻ መሆኑን ከመጽሐፍ ቅዱስ ተምራለች።

“አሁን፣ ዓለምን መለወጥ እንዳለብኝ አይሰማኝም”

የለውጥ አራማጅ የነበረ አንድ ሰው፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ለሰው ዘር እውነተኛ ለውጥ ሊመጣ የሚችልበትን መንገድ ለማወቅ ያስቻለው እንዴት ነው?

መሣሪያዬን ጣልኩ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው የሚያጽናና መልእክት፣ ሲንዲ አስቸጋሪ ባሕርይዋን እንድታስተካክል የረዳት እንዴት ነው?

አምላክ እንደሌለ ይሰማኝ ነበር

በወጣትነቱ በአምላክ የለሽነትና በኮሚኒዝም ጽንሰ ሐሳቦች ይመራ የነበረ አንድ ሰው ለመጽሐፍ ቅዱስ አክብሮት ሊያዳብር የቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል—ኅዳር 2012

ጥሩ ገቢ የሚያስገኝ ሥራ የነበራት ሴት፣ ቁማርተኛ የነበረ ሰው እንዲሁም የሕይወት ትርጉም ጠፍቶት የነበረ ሰው እውነተኛ ደስታ ማግኘት የቻሉት እንዴት ነው?

እምነታቸውን የለወጡት ለምንድን ነው?

“በጣም ብዙ ጥያቄ ነበረኝ”

የቤተ ክርስቲያን ፓስተር የነበረው ማሪዮ የይሖዋ ምሥክሮች እውነቱን እንደሚያስተምሩ ያሳመነው ምንድን ነው?

ለነበሩኝ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አጥጋቢ መልስ አገኘሁ

ማይሊ ጉንደል አባቷ ሲሞት በአምላክ ማመኗን አቆመች። ታዲያ ዳግመኛ በአምላክ ማመን እና ውስጣዊ ሰላም ማግኘት የቻለችው እንዴት ነው?

ጥያቄዎቼን በሙሉ የመለሱልኝ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው!

ኢሶሊና ላሜላ መጀመሪያ የካቶሊክ መነኩሲት በኋላም ኮሚኒስት በመሆን ዓላማ ያለው ሕይወት ለመምራት ጥረት ስታደርግ ነበር፤ ሆኖም አልተሳካላትም። ከጊዜ በኋላ ግን ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ስትገናኝ ዓላማ ያለው ሕይወት መምራት ስለምትችልበት መንገድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አስረዷት።

‘ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ዕንቁ’ አግኝተዋል

ሜሪ እና ብዮርን ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸውን እውነት ያገኙበት መንገድ ይለያያል። ሆኖም ያገኙት ውድ ሀብት ሕይወታቸውን ቀይሮታል። እንዴት?

በሃይማኖት ተስፋ ቆርጬ ነበር

ቶም በአምላክ ማመን ቢፈልግም በዘልማድ የሚፈጸሙ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶችን ማየት ተስፋ አስቆርጦት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስን መማሩ የተስፋ ብርሃን የፈነጠቀለት እንዴት ነው?

“ይሖዋ አልረሳኝም”

ይህቺ ሃይማኖተኛ ሴት ‘ሰዎች የሚሞቱ ለምንድን ነው?’ እና ‘ከሞቱስ በኋላ ምን ይሆናሉ?’ ለሚሉት ጥያቄዎቿ ከጊዜ በኋላ መልስ አገኘች። እውነት ሕይወቷን የለወጠው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

“ቄስ የመሆን ፍላጎት ነበረኝ”

ሮቤርቶ ፓቼኮ በልጅነቱ የካቶሊክ ቄስ የመሆን ፍላጎት ነበረው። ሕይወቱ እንዲለወጥ ያደረገው ምን እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

“እውነቱ ምን እንደሆነ ራሴ እንዳረጋግጥ ፈልገው ነበር”

ሉዊስ አሊፎንሶ የሞርሞን ሃይማኖት ሚስዮናዊ የመሆን ግብ ነበረው። መጽሐፍ ቅዱስን መማሩ ግቡና ሕይወቱ እንዲለወጡ ያደረገው እንዴት ነው?

ዕፅ እና አልኮል መጠጥ

“አሁን የዓመፅ ባሪያ አይደለሁም”

ማይክል ኬንዘል አዲስ ሥራ በጀመረበት ዕለት አንድ ሰው “በዓለም ላይ ለሚታየው መከራ ተጠያቂው አምላክ ነው?” ብሎ ጠየቀው። ይህም ሕይወቱን የሚቀይር አጋጣሚ ሆነ።

ሕይወቴ ከቁጥጥሬ ውጭ ነበር

ሰለሞኔ የተሻለ ሕይወት ለመምራት በማሰብ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሄደ። ሆኖም ዕፅ መውሰድ ጀመረ እንዲሁም እስር ቤት ገባ። ሕይወቱን እንዲያስተካክል የረዳው ምንድን ነው?

የምኖረው ጎዳና ላይ ነበር

አንቶኒዮ በዕፅና በአልኮል ሱስ እንዲሁም በዓመፅ የተጠላለፈ ሕይወት መምራቱ ሕይወት ምንም ዓላማ እንደሌለው እንዲሰማው አድርጎታል። አመለካከቱን እንዲቀይር ያደረገው ምንድን ነው?

ለራሴም ሆነ ለሴቶች አክብሮት ማሳየትን ተማርኩ

ጆሴፍ ኢሬንቦጌን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያነበበው ነገር ሕይወቱን እንዲለውጥ ረድቶታል።

“ሕይወቴ ወዴት አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ በቁም ነገር ማሰብ ጀመርኩ”

አንድ ሰው አምላክን ለማስደሰት ሲል መጥፎ ልማዶቹንና አስተሳሰቡን እንዲለውጥ መጽሐፍ ቅዱስ የረዳው እንዴት እንደሆነ ማንበብ ትችላለህ።

በሕይወቴ ተመረርኩ

ዲሚትሪ ኮርሹኖቭ የአልኮል ሱሰኛ ነበር፤ በኋላ ላይ መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ ማንበብ ጀመረ። በሕይወቱ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ እንዲያደርግ የረዳው ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል—ጥቅምት 2012

ይህ ርዕስ የሁለት ሰዎችን ታሪክ ይዟል፤ እነዚህ ሰዎች የአልኮል መጠጥና የአደንዛዥ ዕፅ ሱሰኝነትን ጨምሮ መጥፎ ልማዶቻቸውን እርግፍ አድርገው በመተው ደስተኛ ሕይወት መምራት የጀመሩት እንዴት ነው?

“በመጨረሻ እውነተኛ ነፃነት አግኝቻለሁ”

አንድ ወጣት ከትንባሆና ከዕፅ እንዲርቅ እንዲሁም ከመጠን በላይ መጠጣቱን እንዲያቆም መጽሐፍ ቅዱስ የረዳው እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ወንጀል እና ዓመፅ

‘ወንጀልና የገንዘብ ፍቅር ብዙ ሥቃይ አስከትሎብኛል’

አርታን ከእስር ከተለቀቀ በኋላ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገንዘብ ፍቅር የሚናገረው ነገር እውነት እንደሆነ ተገንዝቧል።

“አሁን ጨካኝ ሰው አይደለሁም”

ሴባስትያን ካዪራ ዓመፀኝነቱን እንዲተው ያነሳሳው ምንድን ነው?

“የገዛ መቃብሬን እየቆፈርኩ ነበር”

በኤል ሳልቫዶር የሚኖር ቀደም ሲል የወሮበሎች ቡድን አባል የነበረ ሰው በሕይወቱ ውስጥ ለውጥ እንዲያደርግ ያነሳሳው ምንድን ነው?

ለሰዎች ያለኝ አመለካከት ተቀይሯል

ሶባንቱ ሶንቲ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ሲማር ዓመፀኛነቱን ተወ። አሁን በአካባቢው ለሚገኙ ሰዎች ወደፊት ከወንጀልና ከዘራፊዎች ነፃ የሆነ ዓለም እንደሚመጣ እያስተማረ ነው።

ቁጣዬን መቆጣጠር አልችልም ነበር

የወንጀለኞች ቡድን አባል የነበረ አንድ ግለሰብ፣ ያደረገው ለውጥ መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን የሰዎችን ሕይወት የመለወጥ ኃይል የሚያሳይ ማስረጃ እንደሆነ ይሰማዋል። ይህ ሰው በአሁኑ ወቅት ከአምላክ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት መሥርቷል።

ሕይወት የመረረውና ዓመፀኛ ሰው ነበርኩ

በሜክሲኮ የሚኖረው ተደባዳቢ በሕይወቱ ላይ ለውጥ እንዲያደርግ የረዳው ምንድን ነው?

ለአንድ ዓመት ሰላምና ደስታ እንዲሰጠኝ ጸለይኩ

አላን ብሮጂዮ፣ በአንደኛ ዮሐንስ 1:9 ላይ የሚገኘውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲያነብ ልቡ ተነካ።

በሕይወቴ የቀረብኝ ነገር እንደሌለ ይሰማኝ ነበር

ፓቬል ፒዛራ ዓመፀኛና የዕፅ ሱሰኛ የነበረ ከመሆኑም ሌላ በሕግ ትምህርት ትልቅ ቦታ ላይ ለመድረስ ምኞት ነበረው። ሆኖም ከስምንት ሰዎች ጋር በተጣላበት ጊዜ በሕይወቱ ላይ ለውጥ ለማድረግ ተነሳሳ።

ሕይወቴ ከድጡ ወደ ማጡ ሄዶ ነበር

ስቲቨን መክዱወል ዓመፀኛ ወጣት የነበረ ቢሆንም ጓደኞቹ የፈጸሙት የግድያ ወንጀል በሕይወቱ ላይ ለውጥ እንዲያደርግ አነሳሳው።

ይሖዋ መሐሪና ይቅር ባይ እንደሆነ ተማርኩ

ኖርማን ፔልቲዬ ሰዎችን ማታለል እንደ ሱስ ሆኖበት ነበር። ይሁንና ከመጽሐፍ ቅዱስ አንድ ጥቅስ ሲያነብ ያለበት አሳሳቢ ሁኔታ አስለቀሰው።

ከፍትሕ መዛባትና ከዓመፅ ጋር የራሴን ትግል አደርግ ነበር

አንትዋን ቱማ ከንግ ፉ በሚባለው የማርሻል አርት መስክ ሠልጥኖ ነበር፤ ሆኖም በ1 ጢሞቴዎስ 4:8 ላይ የሚገኘው ሐሳብ ሕይወቱን ቀየረው።

መሣሪያዬ ምንጊዜም ከእኔ አይለይም ነበር

አኑንሲያቶ ሉጋራ ዓመፀኛ የወሮበላ ቡድን አባል ነበር፤ ወደ መንግሥት አዳራሽ መሄዱ ሕይወቱን ለወጠው።

“ብዙ ሰዎች ይጠሉኝ ነበር”

ግልፍተኛ የነበረ አንድ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ሰላማዊ እንዲሆን የረዳው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

ስፖርት፣ ሙዚቃ እና መዝናኛ

ጄሰን ዎርድስ፦ ይሖዋን ስታገለግል ምንጊዜም አሸናፊ ነህ

ይሖዋን በማገልገል ላይ ያተኮረ ሕይወት ሁልጊዜም እውነተኛና ዘላቂ ደስታ ያስገኛል።

አንድሬ ኔስማቺኒ፦ እግር ኳስ ሕይወቴ ነበር

ዝና እና ገንዘብ የነበረው ቢሆንም ከዚያ የሚበልጥ ነገር አግኝቷል።

የምፈልገው ነገር በሙሉ ያለኝ ይመስለኝ ነበር

ስቴፈን ገና በወጣትነቱ ስኬታማና ታዋቂ ሙዚቀኛ ሆኖ ነበር። በውስጡ ግን የባዶነት ስሜት ይሰማዋል። ታዲያ ደስተኛ መሆንና ዓላማ ያለው ሕይወት መምራት የቻለው እንዴት ነው?

ያገኘሁት ከሁሉ የሚበልጥ ሽልማት

ፕሮፌሽናል ቴኒስ ተጫዋች የነበረ ሰው ወንጌላዊ ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያስተምር ያነሳሳው ምንድን ነው?

“ማርሻል አርት በጣም እወድ ነበር”

ኢርዊን ላምስፈስ በአንድ ወቅት ጓደኛውን “የተፈጠርንበት ዓላማ ምን እንደሆነ አስበህ ታውቃለህ?” በማለት ጠይቆት ነበር። ጓደኛው ለዚህ ጥያቄ የሰጠው መልስ ሕይወቱን ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል።

ብዙ ጊዜ ብሸነፍም በመጨረሻ ተሳካልኝ

ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱሱን አሸንፎ አምላክ የሚሰጠውን የአእምሮ ሰላም ሊያገኝ የቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል—ሚያዝያ 2013

ኤሳ በሙዚቃው ዓለም ስኬት ቢያገኝም ሕይወቱ ትርጉም እንደሌለው ተሰማው። ይህ የሄቪ ሜታል ሙዚቀኛ እውነተኛ ደስታ ያገኘው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

ጥንካሬ የሚገኘው ይሖዋን በማገልገል ነው

አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፣ ሄርክዩሊስ የግልፍተኝነት ባሕርዩን ለውጦ የተረጋጋና አፍቃሪ መሆን እንደሚችል አረጋግጦለታል።

ከምንም ነገር በላይ የሚያስደስተኝ ቤዝቦል መጫወት ነበር!

ሳሙኤል ሃሚልተን ከምንም በላይ የሚያስደስታቸው ቤዝቦል መጫወት ነበር፤ ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናታቸው ሕይወታቸው እንዲለወጥ አድርጓል።

“ምድር ገነት እንደምትሆን የሚገልጸው ተስፋ ሕይወቴን ለወጠው”

ኢቫርስ ቪጉሊስ በሕይወቱ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በሞተር ሳይክል ውድድር ለሚያገኘው ዝና፣ ክብርና ደስታ ነበር። የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በሕይወቱ ላይ ለውጥ ያመጣው እንዴት ነው?