በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ገንዘብ የሚከፈላቸው የሃይማኖት መሪዎች አሏቸው?

የይሖዋ ምሥክሮች ገንዘብ የሚከፈላቸው የሃይማኖት መሪዎች አሏቸው?

 በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖችን ምሳሌ ስለምንከተል በይሖዋ ምሥክሮች ዘንድ ቀሳውስትና ምዕመናን የሚባል መከፋፈል የለም። ሁሉም የተጠመቁ የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ አገልግሎት ይሰጣሉ፤ እንዲሁም በስብከቱና በማስተማሩ ሥራ ይካፈላሉ። የይሖዋ ምሥክሮች እያንዳንዳቸው ወደ 100 ገደማ የሚሆኑ አማኞችን ባቀፉ ጉባኤዎች ተደራጅተዋል። በጉባኤዎቹ ውስጥ የሚገኙ በመንፈሳዊ የጎለመሱ ወንዶች “ሽማግሌዎች” በመሆን ያገለግላሉ። (ቲቶ 1:5) እንዲህ የመሰለውን አገልግሎት የሚሰጡትም ገንዘብ ተከፍሏቸው አይደለም።