በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽኖች

እነዚህ አጫጭር የአኒሜሽን ቪዲዮዎች አሳሳቢ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት አዝናኝ በሆነ መንገድ ቁም ነገር ያስጨብጣሉ!

 

ሐቀኝነት ያዋጣል?

ስኬታማ ለመሆን የግድ መዋሸት ያስፈልግሃል? ሐቀኛ መሆን ምን ጥቅም እንዳለው እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

አስተዋይ ሁን—ንጽሕናህን ጠብቅ

ንጹሕና የተደራጁ መሆን ጥቅሙ ለአንተ ብቻ ሳይሆን በዙሪያህ ላሉ ሰዎችም ነው። ጤናማ ያደርግሃል፤ ውጥረትም ይቀንስልሃል።

መድልዎ ምንድን ነው?

መድልዎ በታሪክ ዘመናት ሁሉ የሰው ልጆችን ሲያጠቃ ቆይቷል። ይህ በሽታ በውስጥህ ሥር እንዳይሰድ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ተግባራዊ አድርግ።

ራስህን ከተሳሳተ መረጃ ጠብቅ

የሰማኸውን ወይም ያነበብከውን ነገር ሁሉ አትመን። መረጃን መፈተንና ሐሰት የሆነውን መለየት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የገንዘብ አያያዝ

የገንዘብ አያያዝ ከተማርክ ሲያስፈልግህ ገንዘብ አታጣም!

ስታጨስ እንዳትጨስ

ብዙ ሰዎች ትንባሆ ወይም የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ያጨሳሉ፤ ሆኖም ብዙዎች ከዚህ ልማድ ተላቀዋል ወይም ለመላቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። ለምን? ማጨስ ይህን ያህል ጎጂ ነው?

የቪዲዮ ጌሞች፦ እያሸነፍክ ነው እየተሸነፍክ?

የቪዲዮ ጌሞች አዝናኝ ናቸው፤ ግን ጉዳት ሊኖራቸው ይችላል። ጉዳት ሳይደርስብህ አሸናፊ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

ሐዘንን አሸንፎ ደስተኛ መሆን

ከባድ ሐዘን የሚሰማህ ከሆነ ምን ማድረግ ትችላለህ?

ስፖርታዊ ጨዋታዎችን በተመለከተ ምን ማወቅ ይኖርብሃል?

ስፖርት፣ ተባብሮ የመሥራትና የመግባባት ችሎታን ጨምሮ የተለያዩ ክህሎቶችን እንድታዳብር ይረዳሃል። ሆኖም ስፖርት በሕይወትህ ውስጥ ትልቅ ቦታ ከምትሰጣቸው ነገሮች መካከል አንዱ መሆን ይኖርበታል?

መጠጣት የሚያስከትለውን መዘዝ አስብ

ብዙ ሰዎች አልኮል ሲጠጡ በኋላ ላይ የሚቆጩበትን ነገር ያደርጋሉ ወይም ይናገራሉ። አንተስ የአልኮል መጠጥ ከሚያስከትላቸው መዘዞች መራቅ የምትችለው እንዴት ነው?

ወላጆቼን ማነጋገር የምችለው እንዴት ነው?

መናገር በማያሰኝህ ጊዜም እንኳ ከወላጆችህ ጋር መነጋገር የምትችለው እንዴት ነው?

የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ሕይወትህን እየተቆጣጠሩት ነው?

የምትኖረው በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች የተሞላ ዓለም ውስጥ ቢሆንም የመሣሪያዎቹ ባሪያ መሆን የለብህም። የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ሱሰኛ መሆን አለመሆንህን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው? ከዚህ ሱስ ለመላቀቅስ ማን ማድረግ ትችላለህ?

የበለጠ ነፃነት ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?

ወላጆችህ እንደ ትልቅ ሰው ሊያዩህ እንደሚገባ ይሰማህ ይሆናል፤ እነሱ ግን እንደዛ አይሰማቸውም። የወላጆችህን አመኔታ ለማትረፍ ምን ማድረግ ትችላለህ?

ሐሜትን ማስወገድ የምችለው እንዴት ነው?

ጨዋታችሁ ወደ ሐሜት እንደተቀየረ ካስተዋልክ ወዲያውኑ እርምጃ ውሰድ!

እውነተኛ ፍቅር ነው ወይስ የወረት?

በእውነተኛ ፍቅርና በወረት ፍቅር መካከል ምን ልዩነት አለ?

በእኩዮች ተጽዕኖ አትሸነፍ!

የራስህ አቋም ያለህ ሰው ለመሆን የሚረዱ አራት ቀላል ዘዴዎች ቀርበውልሃል።

ማኅበራዊ ድረ ገጾችን ስትጠቀም አስተዋይ ሁን

በኢንተርኔት አማካኝነት ከጓደኞችህ ጋር ስትገናኝ አስተዋይ ሁን።

እውነተኛ ጓደኛ የሚባለው ምን ዓይነት ጓደኛ ነው?

አስመሳይ ጓደኛ ማግኘት ቀላል ነው፤ ይሁን እንጂ እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ቡጢ ሳትሰነዝር ጉልበተኞችን ማሸነፍ

ጉልበተኞች ጥቃት የሚያደርሱት ለምንድን ነው? ጥቃቱን ማሸነፍ የምትችለው እንዴት ነው?