በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ ፍቺን ይፈቅዳል?

መጽሐፍ ቅዱስ ፍቺን ይፈቅዳል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አዎ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ፍቺን ይፈቅዳል። ይሁንና ትዳርን ማፍረስ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው የሚችለው በአንድ ምክንያት ብቻ ነው፤ ይህንንም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ገልጾታል፦ “በዝሙት [ከትዳር ውጭ በሚፈጸም የፆታ ግንኙነት] ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሚስቱን ፈቶ ሌላ የሚያገባ ሁሉ ምንዝር ይፈጽማል።”—ማቴዎስ 19:9

አምላክ በተንኮልና በማታለል የሚፈጸም ፍቺን ይጠላል። ትዳራቸውን በማይረባ ምክንያት የሚያፈርሱ በተለይ ደግሞ ከሌላ ሰው ጋር ለመኖር ሲሉ የትዳር ጓደኛቸውን የሚተዉ ሰዎች በአምላክ ፊት ተጠያቂ ከመሆን አያመልጡም።—ሚልክያስ 2:13-16፤ ማርቆስ 10:9