በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስ ፅንስ ማስወረድን በተመለከተ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ፅንስ ማስወረድን በተመለከተ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሕይወት በአምላክ ፊት ቅዱስ ነው፤ በማህፀን ውስጥ ያለን ፅንስ እንኳ አምላክ እንደ አንድ ሕያው አካል አድርጎ ይመለከተዋል። ንጉሥ ዳዊት በመንፈስ መሪነት “ዐይኖችህ ገና ያልተበጀውን አካሌን አዩ” በማለት ስለ አምላክ ተናግሯል። (መዝሙር 139:16) አምላክ፣ ባልተወለደ ሕፃን ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሰው ተጠያቂ እንደሚሆን ተናግሮ ነበር። በመሆኑም አምላክ፣ ፅንስ ማስወረድን ሕይወት ከማጥፋት ለይቶ አያየውም።—ዘፀአት 20:13፤ 21:22, 23 የ1954 ትርጉም

ይሁን እንጂ አንዲት እናት በምትወልድበት ወቅት ድንገተኛ ሁኔታ ቢፈጠርና ከእናትየው ወይም ከሕፃኑ በሕይወት ማትረፍ የሚቻለው አንዳቸውን ብቻ ቢሆን ምን ማድረግ ይቻላል? በዚህ ጊዜ የማንን ሕይወት ለማትረፍ መሞከሩ የተሻለ እንደሚሆን ባልና ሚስቱ መወሰን ይኖርባቸዋል።