በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አምላክ ስም አለው?

አምላክ ስም አለው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ሰዎች ሁሉ የግል መጠሪያ ስም አላቸው። ታዲያ አምላክ የራሱ የሆነ ስም ሊኖረው አይገባም? ሰዎች፣ እርስ በርስ ወዳጅነት መመሥረት እንድንችል የየራሳችን መጠሪያ ሊኖረን እንዲሁም በዚህ ስም ልንጠቀም ይገባል። ታዲያ ከአምላክ ጋር ለሚኖረን ዝምድናስ ሁኔታው ከዚህ የተለየ መሆን አለበት?

 አምላክ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ “እኔ ይሖዋ ነኝ። ስሜ ይህ ነው” ብሏል። (ኢሳይያስ 42:8 NW) አምላክ “ኤልሻዳይ፣” “ሉዓላዊ ጌታ” እና “ፈጣሪ” እንደሚሉት ያሉ በርካታ የማዕረግ ስሞች ቢኖሩትም ታማኝ አገልጋዮቹ በግል ስሙ እንዲጠሩት በመፍቀድ አክብሯቸዋል።—ዘፍጥረት 17:1፤ የሐዋርያት ሥራ 4:24፤ 1 ጴጥሮስ 4:19

 በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በዘፀአት 6:3 ላይ የአምላክን ስም ይጠቅሳሉ። ጥቅሱ በ1879 ትርጉም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ይላል፦ “ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ (ኤልሻዳይ) ተገለጥሁ በስሜም እግዚእ (ይሖዋ) አልታወቅሁላቸውም።”

 ይሖዋ፣ ለዘመናት ተቀባይነት አግኝቶ የቆየ የአምላክ ስም አጠራር ነው። በርካታ ምሁራን “ያህዌህ” የሚለውን አጠራር ቢመርጡም ይሖዋ (በእንግሊዝኛ ጀሆቫ) የሚለው አጠራር በስፋት ይታወቃል። የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተጻፈው በእንግሊዝኛ ሳይሆን በዕብራይስጥ ነው፤ ይህ ቋንቋ የሚነበበው ደግሞ ከቀኝ ወደ ግራ ነው። በዕብራይስጥ ቋንቋ ይህ ስም በአራት ተነባቢ ፊደላት (יהוה) ተጽፎ ይገኛል። እነዚህ የሐወሐ በሚሉት ፊደላት የሚጻፉት እነዚህ አራት የዕብራይስጥ ሆሄያት ቴትራግራማተን ተብለው ይጠራሉ።