በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የአምላክ ስም ኢየሱስ ነው?

የአምላክ ስም ኢየሱስ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ኢየሱስ ስለ ራሱ ሲናገር “የአምላክ ልጅ” በሚለው መጠሪያ ይጠቀም ነበር። (ዮሐንስ 10:36፤ 11:4) ኢየሱስ መቼም ቢሆን ሁሉን ቻይ አምላክ እንደሆነ ተናግሮ አያውቅም።

 ከዚህም በተጨማሪ ኢየሱስ ወደ አምላክ ጸልዮአል። (ማቴዎስ 26:39) ተከታዮቹን እንዴት እንደሚጸልዩ ሲያስተምራቸውም “በሰማያት የምትኖር አባታችን፣ ስምህ ይቀደስ” እንዲሉ ነግሯቸዋል።—ማቴዎስ 6:9

 ኢየሱስ “እስራኤል ሆይ ስማ፣ ይሖዋ አምላካችን አንድ ይሖዋ ነው” የሚለውን ጥቅስ በተናገረበት ወቅት የአምላክ ስም ማን እንደሆነ በግልጽ ጠቁሟል።—ማርቆስ 12:29፤ ዘዳግም 6:4