በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል?

የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የአምላክ መንግሥት፣ ሁሉንም ሰብዓዊ መንግሥታት አጥፍቶ መላውን ምድር ይገዛል። (ዳንኤል 2:44፤ ራእይ 16:14) በዚህ ጊዜ የአምላክ መንግሥት . . .

  • በራስ ወዳድነት በሌሎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ክፉ ሰዎችን ያጠፋል። “ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይወገዳሉ።”—ምሳሌ 2:22

  • ጦርነትን ሙሉ በሙሉ ያስቀራል። “[አምላክ] ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል።”—መዝሙር 46:9

  • በምድር ላይ ብልጽግናን እና ሰላምን ያሰፍናል። “እያንዳንዱ ሰው በተከለው ወይንና በለስ ጥላ ሥር በሰላም ይኖራል፤ የሚያስፈራውም ነገር አይኖርም።”—ሚክያስ 4:4 የ1980 ትርጉም

  • ምድርን ወደ ገነትነት ይለውጣል። “ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፤ በረሓው ሐሤት ያደርጋል፤ ይፈካል፤ እንደ አደይም ያብባል።”—ኢሳይያስ 35:1

  • እያንዳንዱ ሰው ትርጉም ያለውና አስደሳች ሥራ እንዲኖረው ያደርጋል። “[አምላክ የመረጣቸው ሰዎች] በእጃቸው ሥራ ለረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል። ድካማቸው በከንቱ አይቀርም።”—ኢሳይያስ 65:21-23

  • በሽታን ያጠፋል። “‘ታምሜአለሁ’ የሚል አይኖርም።”—ኢሳይያስ 33:24

  • እርጅናን ያስወግዳል። “ሥጋው እንደ ሕፃን ልጅ ገላ ይታደሳል፤ ወደ ወጣትነቱም ዘመን ይመለሳል።”—ኢዮብ 33:25

  • የሞቱ ሰዎችን ያስነሳል። ‘በመታሰቢያ መቃብር ያሉ ሁሉ የኢየሱስን ድምፅ ሰምተው ይወጣሉ።’—ዮሐንስ 5:28, 29